በኮሮና ቫይረስ የተጠቁት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ማገገማቸው ተገለጸ
ጆ ባይደን በኮሮና ቫይረስ ሲጠቁ ለሁለተኛ ጊዜ ነው
![](https://cdn.al-ain.com/images/2022/7/25/243-212202-donneee_700x400.jpg)
ፕሬዝዳንቱ ከአራት ቀናት በፊት በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ይታወሳል
በኮሮና ቫይረስ የተጠቁት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ማገገማቸውን የፕሬዝደንት ባይደን ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከአራት ቀናት በፊት በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸውን የነጩ ቤተመንግስት ቃል አቀባይ ጽህፈት አሳውቆ ነበር።
ጽህፈት ቤቱ የፕሬዝዳንቱን ሐኪም ዋቢ አድርጎ ባወጣው መግለጫ ፕሬዝዳንት ባይደን ከቫይረሱ ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም አገግመዋል ተብሏል።
ፕሬዝዳንቱ ጉሮሯቸውን ከሚከረክራቸው የተወሰነ ህመም ስሜት ውጪ በተሻለ ጤና ላይ እንደሆኑም ተገልጿል።
የህክምና ቡድኑ ለፕሬዝዳንቱ ክትትል እያደረገ መሆኑን ያሳወቀው ጽህፈት ቤቱ አሁን ላይ ምንም አይነት የአተነፋፈስ ችግር የለባቸውም ተብሏል ።
ፕሬዝዳንት ባይደን ቫይረሱ ከተገኘባቸው ጊዜ አንስቶ ራሳቸውን አግለው ስራቸውን በማከናወን ላይ እንደሆኑ መናገራቸው ይታወሳል።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከዚህ በፊት በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው የነበረ ሲሆን በድጋሚ ከአራት ቀናት በፊት ዳግም ተይዘዋል።
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዚሁ ኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው ማገገማቸው ይታወሳል።
ኮሮና ቫይረስ የበርካታ ሀገራት መሪዎችን ያጠቃ ሲሆን የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ፣ የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ቦልሴናሮ እና ሌሎችም ከተጠቁ መሪዎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው።