ቴክኖሎጂው የተቋማትን እና ሰዎችን ምርታማነት ቢጨምርም በዛው ልክ ስራቸውን የሚቀማቸው ሰዎች አሉ ተብሏል
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የማይተኩ 10 ሙያዎች ምን ምን ናቸው?
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሚባለው ቴክኖሎጂ የሰው ልጆችን የዕለት ተዕለት ስራዎች በማቅለል ላይ ይገኛል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ግን በኤአይ ምክንያት ከስራ ውጪ የሚሆኑ የሙያ መስኮች እንዳሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ 300 ሚሊየን የሚደርስ የሰው ልጆችን የሙሉ ጊዜ ስራ ተክቶ መስራት ይችላል ተብሏል።
ይሁንና የተወሰኑ የሙያ መስኮች አሁንም በሰው ሰራሽ አስተውሎት የማይተኩ ሙያዎች ይፋ ሆነዋል፡፡
እንደ ፎርብስ ዘገባ የዳኝነት፣ ጥብቅና፣ እና አመራርነት ሙያዎች ሰው ሰራሽ አስተውሎት የማያሰጋቸው የሙያ መስኮች ተብለዋል፡፡
እንዲሁም የፈጠራ ባለሙያዎች፣ ቴራፒስቶች እና የተለያዩ ሙያ አማካሪዎች ደግሞ በኤአይ ስጋት ውስጥ የሌሉ ሙያዎች ናቸው፡፡
ሌላኛው ሰው ሰራሽ አስተውሎት መዘመን ከማያሰጋቸው ሙያዎች መካከል የመምህርነት ሙያ ሲሆን ነርስ እና የንግድ ሙያም ከሰው ልጆች ውጪ የማይሰሩ የሙያ መስኮች እንደሆኑ ተገልጿል፡፡