አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን ትርፋማነት በእጅጉ እያሳደገ ነው
ኦፕንኤአይ ያስተዋወቀው ቻትጂፒቲ ከተዋወቀ አንድ አመት ከስድስት ወራት ተቆጥረዋል።
እንደ አልፋቤት፣ ማይክሮሶፍት እና አማዞን ያሉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችም ለዘርፉ ቢሊየን ዶላሮችን በመመደብ ፉክክር ከጀመሩ ሰነባብተዋል።
ለዘርፉ ትኩረት የሰጡ ኩባንያዎች የአክሲዮን ገበያው ደርቶላቸው ትርፋማነታቸውም በእጅጉ መጨመሩን ፎርብስ ያወጣው መረጃ ያሳያል።
አሜሪካዊው ቻርለስ ሊያንግም ከሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ከፍተኛውን ገቢ በማስገባት ቀዳሚው ናቸው ተብሏል።
የቻትጂፒቲ መስራች ኩባንያው ኦፕንኤአይ ስራአስፈጻሚ ሳም አልትማንም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ እንዲገቡ ካደረጋቸው መካከል ይጠቀሳሉ።
ፎርብስ በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ በመሰማራት የቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ ገብተዋል በሚል የዘረዘራቸውን ይመልከቱ፦