በቤጂንግ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተሰራችው ይህች አዲስ ፈጠራ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውደርዕይ ላይ ለጎብኚዎች ቀርባለች
የቻይና ሳይንቲስቶች ህጻን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሰሩ፡፡
የወቅቱ የቴክኖሎጂ ፉክክር የሆነው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ወይም ሰው ሰራሽ አስተውሎት በየሀገሩ አዳዲስ ፈጠራዎች ይፋ እየሆኑ ሲሆን ቻይናም የመጀመሪያውን ህጻን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ይፋ አድርጋለች፡፡
የቤጂንግ ጠቅላላ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተሰራችው ይህች ህጻን ሰው ሰራሽ አስተውሎት በአውደርዕይ ላይ ለተመልካቾች ቀርባለች፡፡
ህች ህጻን ከሶስት እስከ አራት ዓመት እድሜ ካላት እውነተኛ የሰው ልጅ ጋር ተቀራራቢ አስተሳሰብ ይኖራታልም ተብሏል፡፡
አዲሱ ፈጠራ የህጻናትን ባህሪ ለማጥናት አይን ገላጭ ይሆናል የተባለ ሲሆን ህች ህጻን የራሷ የሆነ ደስታ፣ ሀዘን እና ንዴት አይነት ስሜቶች እንዳላትም ተገልጿል፡፡
የምንሞትበትን ቀን የሚተነብየው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ
ከዚህ በተጨማሪም ይህች አዲስ ፈጠራ ከሰዎች ጋር መግባባት እንድትችል ተደርጋ ተሰርታለች የተባለ ሲሆን የሰዎችን አካላዊ እንቅስቃሴ እና ቃላት ልውውጥ መሰረት አድርጋ ምላሽ ትሰጣለችም ተብሏል፡፡
የቤጂንግ ጠቅላላ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በቀጣይ ተጨማሪ ማሻሻያዎችን በማድረግ ቀስ በቀስ ሌሎች ፈጠራዎችን ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል፡፡
ለዓለማችን ስጋት ሆናል የተባለው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጥብቅ ቁጥጥር ካልተደረገበት ለሰው ልጆች መጥፋት ምክንት ሊሆን እንደሚችል ተመራማሪዎች በተደጋጋሚ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል፡፡
በፈረንጆቹ 2050 ላይም 40 በመቶ የዓለማችን ስራዎች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እንደሚያዙ ከአንድ ወር በፊት የተካሄደው የዓለም ኢኮኖሚ ጉባኤ አስታውቆ ነበር፡፡