በጆርዳን የ42 አመቱ ጎልማሳ ነፍሰ ጡር ሆኖ ተገኘ
በመካከለኛው ምስራቋ ሀገር ጆርዳን ያጋጠመው ክስተት ዓለምን እያነጋገረ ይገኛል፡፡
ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ የ42 ዓመቱ ጆርዳናዊ ህመም ተሰምቶች ወደ ህክምና ተቋም ሲሄድ በተደረገለት ተደጋጋሚ ምርመራ ነፍሰ ጡር እንደሆነ በቤተ ሙከራ ምርመራ ይረጋገጣል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ሀኪሞች እና ታማሚውን ጨምሮ ብዙዎች ቢገረሙም ጉዳዩ ትኩረት እንደሚፈልግ ይገለጻል፡፡
በተለይም ግለሰቡ እንዴት ነፍሰ ጡር ሊሆን ቻለ፣ ነፍሰ ጡር ከሆነስ ስለምን ጽንስ ሊገኝ አልቻለም የሚሉ ጥያቄዎች መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
በተደረጉ ተጨማሪ ምርመራዎችም ጎልማሳው ግለሰብ ነፍሰ ጡር እንደሆነ የምርመራ ውጤቱ ይናገር እንጂ እንደተባለው በሆዱ ጽንስ ስለመኖሩ ማረጋገጥ ሳይቻል ይቀራል፡፡
እንደ አል አረቢያ ዘገባ ከሆነ በግለሰቡ ጣፊያ ላይ የሆርሞን ለውጥ መታየቱ ግለሰቡ የእርግዝና ስሜት እንዲሰማው እና የምርመራ ውጤቱም ነፍሰ ጡር እንደሆነ የሚያሳይ እንዲሆን ምክንያት መሆኑን ሀኪሞች ይደርሱበታል፡፡
በግለሰቡ ጣፊያ ላይ የተፈጠረው አነስተኛ እባጭ መሳይ አካል ወደ ጉበቱም አምርቶ ለተፈጠረው የጤና ችግር ዋነኛ መነሻ ሆኖ ተገኝቷል ተብሏል፡፡
ይህ መሳይ የጡና እክል ያልተለመደ እና ጭራሽኑ ሊያጋጥም ይችላል ተብሎ እንደማይጠበቅም አል አረቢያ የህክምና ባለሙያዎችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡