ከ12 ሚስቶች 102 ልጆችን ያገኙት ኡጋንዳዊ የኑሮ ውድነት ቤተሰቤ እንዳይስፋፋ ገድቦታል አሉ
568 የልጅ ልጆች ያሉት የ67 አመት ጎልማሳ፥ “ገቢዬ ከኑሮ ውድነቱ አንጻር መዳከሙ ሰፊውን ቤተሰብ የሚቀላቀሉ ተጨማሪ ልጆች እንዳይኖሩ አድርጓል” ብለዋል
ሚስቶቻቸውም የወሊድ መቆጣጠሪያ እንዲጠቀሙ ማዘዛቸው ነው የተሰማው
ከ12 ሚስቶች 102 ልጆችን ያገኙት ኡጋንዳዊ የኑሮ ውድነት ቤተሰቤ እንዳይስፋፋ ገድቦታል አሉ
ኡጋንዳዊው አርሶ አደር 102 ልጆችን ከ12 ሚስቶቻቸው አግኝተዋል፤ የልጅ ልጆቻቸው ቁጥርም 568 ደርሷል።
የ67 አመቱ ጎልማሳ ተጨማሪ ልጆችን እንዳይወልዱና ቤተሰቡ እንዳይስፋፋ የኑሮ ውድነት ፈተነኝ እያሉ ነው።
“ገቢዬ ከኑሮ ውድነቱ አንጻር መዳከሙ ሰፊውን ቤተሰብ የሚቀላቀሉ ተጨማሪ ልጆች እንዳይኖሩ አድርጓል” ማለታቸውንም ዴይሊ ሜል አስነብቧል።
ሙሳ ሃሳይሃ የተባሉት ጎልማሳ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት በሚፈቀድባት ሉሳካ ከተማ ነው የሚኖሩት።
12 ሚስቶች፣ 102 ልጆች እና 586 የልጅ ልጆቻቸው በአጠቃላይ 700 ቤተሰብን የሚያሰተዳድሩት ጎልማሳ አሁን አቅም አጥተዋል።
ገቢዬ ከኑሮ ዋጋ መናር ጋር የሚመጣጠን አልሆንልህ አለኝ እያሉ ነው።
ከ102 የሃሳይሃ ልጆች ሲሶው አብረዋቸው እንደሚኖሩና አብዛኞቹ የልጅ ልጆቻቸውም የሳቸውን እጅ እንደሚጠብቁ ነው ያነሱት።
“ሚስቶቼን በአንድ ላይ ነው የማኖራቸው፤ ይህም ሌሎች ወንዶች እንዳይተናኮሏቸው ለመቆጣጠር ያግዘኛል” የሚሉት ጎልማሳ፥ ሚስቶቻቸው የወሊድ መቆጣጠሪያ እንዲጠቀሙ አዘዋል።
የሃሳይሃ 11 ልጆች እናት ዙላይካም “ከዚህ በኋላ ልጅ አልወልድም፤ የባለቤቴን መቸገር እየተመለከትኩ መውለድ ስለሌለብኝ የወሊድ መቆጣጠሪያ እየወሰድኩ ነው” ብለዋል።
የልጆቻቸው እድሜ ከስድስት እስከ 51 ይደርሳል የተባለ ሲሆን፥ ታላቁ ልጃቸው ወጣቷን ሚስታቸውን በ21 አመት ይበልጣል።
የኑሮዬ ሁኔታ ቢስተካከል ተጨማሪ ልጆችን ከመውለድ የሚያቆመኝ አይኖርም ነበር ያሉት የ67 አመት ጎልማሳ የሚያሳርፋቸው ልጅ ግን ያገኙ አይመስልም።