ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰን ሰበረ
ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰን ሰበረ
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በለንደን የተካሄደውን የቫይታሊቲ ቢግ ግማሽ ማራቶን ውድድርን ክብረ ወሰን በመስበር አሸንፏል።
ቀነኒሳ ውድድሩን 1 ሰዓት ከ 00 ደቂቃ 22 ሰከንድ በመጨረስ በበላይነት አጠናቋል።
በዚህም ቀነኒሳ በቀለ በእንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህ ተይዞ የነበርውን የቫይታሊቲ ቢግ ግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰን ሰብሯል፡፡
ከቀነኒሳ ጋር ብርቱ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ተጠብቆ የነበረው ሞ ፋራህ በህመም ምክንያት ከውድድሩ ውጭ መሆኑን ቀደም ብሎ ማሳወቁ ይታወሳል።
የ5000 እና 10000 ሜትር ውድድሮች የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቱ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በቫይታሊቲ ቢግ ግማሽ ማራቶን ውድድር ሲሳተፍ ይህ የመጀመሪያው ነው።
ምንጭ፡- ቢቢሲ