የኬንያ ጦር ዋና አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦጎላ በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው አለፈ
በሄሊኮፕተር አደጋ የቴንያ ጦር ዋና አዛዡን ጨምሮ 9 የኬንያ ጦር አባላት ሞተዋል
11 የኬንያ ጦር አባላትን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሄሊኮፕተር ዛሬ ከሰዓት ተከስክሷል
የኬንያ መከላከያ ኃይል ዋና አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦሞዲ ኦጎላ በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ማምሻወን በሰጡት መግለጫ፤ “ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ገደማ ላይ አገራችን እጅግ አሳዛኝ የሄሊኮፕተር አደጋ አስተናግዳለች” ብለዋል።
“የሄሊኮፕተር መከስከስ አደጋውም የኬንያ መከላከያ ኃይል ዋና አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦሞዲ ኦጎላ ህይወታቸው ማፉን ስገለጽ በትላቅ ሀዘን ውስጥ ሆኜ ነው” ብለዋል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ።
ሄሊኮፕተሩ የኬንያ መከላከያ ኃይል ዋና አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦሞዲ ኦጎላን ጨምሮ 11 የኬንያ ጦር አባላትን አሳፍሮ በመብረር ላይ እያለ መከስከሱንም ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል።
በአደጋውም የኬንያ ጦር ዋና አዛዥን ጨምሮ የ9 የጤንያ ጦር አባላት ህይወት ማለፉንም ነው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በመግለጫቸው ያስታወቁት።
በተከሰከሰው ሄሊኮፕተር ውስጥ ከነበሩ ተሳፋሪዎች መካል 2 የኬንያ ጦር አባላት በህይወት መትረፋቸውንም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በመግለጫቸው፤ “ኬንያ ውድ ልጇን አጣች” ያሉ ሲሆን፤ እንደ ኬንያ ጦር ጠቅላይ ኣዥነታቸው ከፍተኛ ሀዘን እንደተሰማቸውም ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የብሔራዊ ሀዘን ጊዜ ይፋ ባደረገበት ወቅት "የመላው የኬንያ ህዝብ ከባ ሀዘን ውስጥ ነው" ብለዋል።