1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዜጎቿ በድርቅ የተጋለጡባት ኬንያ የአደጋ ጊዜ አዋጅ አወጀች
በድርቁ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በ6 ወራት ውስጥ ከ2 ሚሊዮን ሊያሻቅብ ይችላል ተብሏል
አዋጁ በፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የታወጀ ነው
የተለያዩ የኬንያ አካባቢዎች በድርቅ ጠቃታቸውን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የአደጋ ጊዜ አዋጅ አወጁ፡፡
ኬንያታ መንግስታቸውን ተጎጂዎችን ለመደገፍ የሚያስችሉ ስራዎችን እንዲሰራ አዘዋል፡፡
በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ድርቅ ምክንያት በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ምናልባትም ከ2 ሚሊዮን የሚልቁ ኬንያውያን ለርሃብ ሊጋለጡ እንደሚችሉ የሃገሪቱ የድርቅ አስተዳደር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
ድርቁ እስካሁን 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኬንያውያንን ማጥቃቱንም ነው ባለስልጣኑ ያስታወቀው፡፡
ኬንያ በእንዲህ ዐይነት የከፋ የድርቅ ሁኔታ የአደጋ ጊዜ አዋጅ ያወጀችው በፈረንጆቹ 2017 ነበር፡፡