በኬንያ ጸረ-መንግስት ተቃውሞዎች ምክንያት ውጥረቱ ተባብሷል
የኬንያ ተቃዋሚ መሪ ተቃውሞዎችን ለማስቆም የቀረበላቸውን ጥሪ ውድቅ አድረጉ፡፡
የኬንያ ተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ለሰኞ የታቀደውን ጸረ-መንግስት ሰልፍ እንዲቆሙ የቀረበላቸውን ጥሪ ውድቅ አድርገዋል።
መንግስት በህዝብ ደህንነት እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን በመጥቀስ ሰልፉን ከልክሏል።
ኦዲንጋ እሁድ እለት "ሁላችንም ተዘጋጅተናል፤ ሰኞ ለታላቅ ሰልፍ ተዘጋጅተናል" ብለዋል።
የኬንያ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪጋቲ ጋቻጓ በሀገሪቱ ለቀጠሉ ሰልፎች ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ለኦዲንጋ ሰጥተዋል ነው የተባለው።
ኢትዮጵያ ለኬንያ የኤሌክትሪክ ሀይል መሸጥ ጀመረች
ምክትል ፕሬዝዳንቱ መንግስት እርምጃ ከመውሰዱ በፊት የሰኞው ተቃውሞው የመጨረሻ እንደሚሆን ተናግረዋል።
"መንግስት ሰኞ ላይ ስልጣኑን አስረግጦ ህይወትን እና ንብረትን ይጠብቃል" ማለታቸውን አናዶሉ ዘግቧል።
በኬንያ ለሳምንታት በቀጠለው ህዝባዊ ተቃውሞ አንድ ፖሊስን ጨምሮ አራት ሰዎች ሲሞቱ፤ በመላ ሀገሪቱ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መታሰራቸውን ባለስልጣናት ገልጸዋል።
ሆኖም የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መንግስት የኑሮ ውድነቱን እንዲቀንስ ለማስገደድ የታቀዱት ጸረ-መንግስት ሰልፎች በተያዘላቸው መርሃ-ግብር እንደሚቀጥሉ ኦዲንጋ ተናግረዋል።
የኃይማኖት መሪዎች እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተቃውሞውን እንዲያቆሙ ጥሪ ቢያደርጉም ኦዲንጋ ሰልፉን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። ስለ መጠለፉ ቀረ ግን ተጠርጥሯል