ኢትዮጵያ ለኬንያ ከምትሸጠው ሀይል በዓመት 100 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት አቅዳለች
ኢትዮጵያ ለኬንያ የኤሌክትሪክ ሀይል መሸጥ መጀመሯን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል እንደገለጸው በኢትዮ- ኬኒያ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዛሬ በይፋ የኤሌክትሪክ ሽያጭ ተጀምሯል።
ከጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ የሙከራ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው የኢትዮ- ኬኒያ ባለ 500 ኪሎ ቮሌት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና የኮንቨርተር ማከፋፈያ ጣቢያ በይፋ ሽያጭ መጀመሩ ተገልጿል።
ይህ የሀይል የማስተላለፊያ መስመር በዓመት እስከ 100 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማስገባት አቅም አለው የተባለ ሲሆን ከኬንያ አልፎ ከታንዛኒያ እስከ ደቡብ አፍሪካ ላሉት ሀገራት እስከ ሁለት ሺህ ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ የማስተላለፍ አቅም እንዳለውም ተቋሙ አስታውቋል።
የኢትዮ- ኬንያ የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና ኮንቨርተር ጣቢያ ፕሮጀክት አአማካሪ ድርጅት፣ ለካሳ ክፍያና የተሰረቁ መሰረተ ልማቶችን ለመተካት የወጣውን ወጪ ጨምሮ 500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶሊር ወጪ ተደርጎበታልም ተብሏል፡፡
ከዚህ ውስጥ 214 ነጥብ 5 ሚሉዮን ዶላሩ የኮንቨርተር ስቴሽኑና ለግራውንድ ኤላክትሮድ መስመር የግንባታ ሥራ እንዲሁም 120 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ ለማስተላለፊያ መስመሩ እንደዋለ ተገልጿል።
የኢትዮ- ኬኒያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመር የግንባታ ሥራ "CET" በተሰኘ የቻይና ኩባንያ የተከናወነ ሲሆን የኮንቨርተር ማከፋፈያ ጣቢያውና የግራውንድ ኤላክትሮድ መስመሩ ደግሞ ሲመንስ በተሰኘ ኩባንያ ተከናውኗል።
በኢትዮጵያ በኩል የተዘረጋው የማስተላለፊያ መስመር እና የፕሮቴክሽንና የዳታ ኮሙዩኒኬሽን መስመር (ኦፕቲካሌ ግራውንድ ፋይበር) 440 ኪል ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን 994 የከፍተኛ ኃይሌ ተሸካሚ የብረትታወሮች አሉት።
ኢትዮጵያ ቀደም ሲሌ ከሱዳን እና ከጅቡቲ ጋር የኃይል ሽያጭ እያካሔደች ሲሆን ከሶማሊ ላንድ፣ ታንዛኒያ፣ደቡብ ሱዳን እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር የኤሌክትሪክ ኃይሌ ሽያጭ ለማከናወን የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሟ ይታወሳል።
ባለፈው ዓመት ከሱዳን እና ጅቡቲ ኤክስፖርት ከተደረገው የኤሌክትሪክ ኃይሌ 95 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶሊር ገቢ መገኘቱን ተቋሙ ከዚህ በፊት አስታውቋል።