በቲክ ቶክ እና በኤክስ የተሰራጨው የኬንያ የፓርላማ አባላት ቅንጡ አኗኗር ባለፈው ወር እየተንተከተከ በነበረው የወጣቾች ቁጣ ላይ ተጨማሪ ማቀጣጠያ ነዳጅ ሆኖ ነበር
የኬንያ የፓርላማ አባላት በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለቋቸው ቅንጡ ኑሯቸውን የሚያሳዩ ፓስቶች የጸረ- ታክስ ተቃውሞው እንዲቀጣጠል አድርገዋል ተብሏል።
ቅንጡ የቤት መኪኖች፣ የግል ጀቶች እና የተትረፈረፈ ገንዘብ።በቲክ ቶክ እና በኤክስ የተሰራጨው የኬንያ የፓርላማ አባላት ቅንጡ አኗኗር ባለፈው ወር እየተንተከተከ በነበረው የወጣቾች ቁጣ ላይ ተጨማሪ ማቀጣጠያ ነዳጅ ሆኖ ነበር።
ለሳምንት የቆየው የታክስ ተቃውሞ፣ 3/4ኛው ወጣት እና ጥሩ ክፋያ ያለው ስራ እጥረት ባለባት ኬንያ ውስጥ ያለው ከፍተኛ የፓርላማ አባላት ደሞዝ እና ቅንጡ ኑሮ ትኩረት እንዲስብ አድርጎታል።
ባለፈው ሰኔ መጨረሻ ተቃውሞው ከፍተኛ ደረጃ በደረሰበት ወቅት፣ የተቆጡ ወጣቶች ወደ ፓርላማ በመግባት የተወሰነውን የፓርላማ ክፍል በእሳት አያይዘዋል፤ እያመለጡ የነበሩ ፓለቲከኞችን በመኪኖች በድንጋይ መትተዋል።
ከእዚያ ጊዜ ጀምሮ በዋናነት የገዥው ፓርቲ ጥምረት ጋር ግንኙነት ያላቸው የፓርላማ አባላት መኖሪያዎች እና ንብረቶች የጥቃት ሰለባ እየሆኑ ነው። በሀገሪቱ ቲክ ቶክ እና ኤክስ የተቃውሞ መቀስቀሻ ሆነዋል።
የፖለቲከኞች መልክቶች አርትኦት ተሰርቶባቸው ከአሉታዊ መልእክት ጋር ይፖሰታሉ።
ሁለቱ የማህበራዊ ሚዲያዎች በኬንያ ገንዘብ እየባከነ ነው በሚሉ አሉባልታዎች ተጥለቅልቀዋል።
ይህ የወጣቶች ተቃዎሞ የተደራጀ አመራር እንደሌለው ይነገራል። ይሁን እንጅ የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊየም ሩቶ "ድምጻችሁን ሰምቻለሁ፤ተሸንፌያሁ" እንዲሉ አስገድዷቸዋል።
በምግብ እና በንጽህና መጠበቃያ እቃዎች ላይ ተጨማሪ ታክስ እንዲጣል የሚያስገድደው የፋይናንስ ረቂቅ ህግ በፓርላማ ቢጸድቅም፣ ህግ እንዲሆን አልፈርምቀትም፤ ቀይ ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል።
ሩቶ መንግስታቸው የወጭ ቅነሳ ፓሊሲ ተግባራዊ እንደሚያደርግ እና ሌሎች አማራጮችን እንደሚፈልግ ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ ተቃውሞውም ረገብ ብሏል።
ፕሬዝዳንቱ ከትናንት በስትያ በሰጡት መግለጫ ካቢኔያቸውን ሙሉ ለሙሉ በትነዋል።
ፕሬዝደንቱ ሐብድር እዳ ጫና ፣ ለኑሮ ውድነት ፣ ለስራ አድል ፈጠራ እና ሌሎችም ችግሮች ላይ መፍትሄ መስጠት የሚችሉ አዳዲስ ካቢኔዎችንም እንደሚያዋቅሩ ግልጽ አድርገዋል።