የብሔራዊ ፓሊስ አገልግሎት እንደገለጸው ፖሊሱ "ባልታወቀ ምክንያት" ወደ ችሎት ገብቷል
አንድ ከፍተኛ የኬንያ ፖሊስ በኬንያ ዋና ከተማ ናይኖቢ በሚገኝ ፍርድ ቤት ውስጥ ዳኛ ላይ ከተኮሰ በኋላ መገደሉን ቢቢሲ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ ዋና ኢንስፔክተሩ የማካድራ ዋና ዳኛ በሆኑት ሞኒካ ኪቩቲ ላይ የተኮሱት ዳኛዋ የፓሊሱ ባለቤት በተከሰሱበት ጉዳይ ውሳኔ ካሳለፉ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ነው።
እኝህ ፖሊስ የተናደዱት ዳኛዋ የባለቤታቸውን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረጋቸው ነው ተብሏል።
በምዕራብ ኬንያ ሎንዲያኒ ውስጥ የሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ የሆኑት ሳምሶን ኪፕቺርቺር ኪፕሩቶ የተባሉት ፓሊስ ጠብመንጃ በማውጣት ወደ ዳኛዋ ተኩሰው እግራቸውን አቁስለዋል።
በችሎቱ ውስጥ ያሉት ሌሎች ፖሊሶች ወዲያውኑ የአጸፋ ምላሽ የሰጡ ሲሆን ከፓሊሶቹ ውስጥ አንደኛው ጥቃት አድራሹን ተኩሶ ገድሏል።
በዚህ ግጭት ሶስት ፓሊሶች የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ፓሊስ ባወጣው ሪፓርት አስታውቋል።
ዳኛዋ እና የቆሰሉት ፓሊሶች ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተደረገላቸው ነው ተብሏል።
ፍርድ ቤቱ ባወጣው መግለጫ ፍርድ ቤቱ ዋስትና ተስጥቶት ለቀረ እና ለቀረበት ምክንያት በቂ ማብራሪያ ማቅረብ ላልቻለ ግለሰብን ዋስተና ይሰርዛል ብሏል።
ፍርድ ቤቱ "ይህ ውሳኔ ይፋ እንደተደረገ ሰውየው(ፖሊሱ) ወደ ዳኛዋ ተኩሶ ጭኗን አቁስሏል" ብሏል በመግለጫው።
መጀመሪያ ላይ በወው ሪፓርት "ተኩስ የከፈተው ተጠርጣሪዋን ያገባው የ ፖሊስ ባልደረባ ነው" አመልክቷል።
የብሔራዊ ፓሊስ አገልግሎት እንደገለጸው ፓሊሱ "ባልታወቀ ምክንያት" ወደ ችሎት ገብቷል። ተኩስ እንዲፈጠር ምክንያት የሆኑ ሁነቶችን ለማወቅ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን አገልግሎቱ ጨምሮ ገልጿል።
በችሎት ውስጥ የተፈጸመው ይህ ክስተት እንዴት ሊሆን ቻለ በሚል ብዙ ኬንያውያን አስደንግጧል።
ፖሊሰ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ የሆነ ግድያ በመፈጸም ቢከሰሰም ፍርድ ቤት ውስጥ እንዲህ አይነት ክስተት እስካሁን አላጋጠጠም።ይህን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ የፍርድ ቤቱን ሰራተኞች ደህንነት ለማስጠበቅ ጥበቃዎችን እንደሚያጠናክር መሆኑን ገልጿል።