ኬንያ ዝቅተኛ የሰራተኞች ደመወዝ ጣሪያን በ12 በመቶ አሳደገች
የኬንያ መንግስት በወሰነው መሻሻያ መሰረት 6 ሺህ 7001 ብር ዝቅተኛው የደመወዝ ጣሪያ ሆኗል
በኬንያ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል 5 ሺህ 983 ብር ነበር
ኬንያ ዝቅተኛ የሰራተኞች ደመወዝ ጣሪያን በ12 በመቶ አሳደገች፡፡
የኬንያ ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እንዳሳወቁት በሀገሪቱ ከዚህ በፊት ተወስኖ የነበረው ዝቅተኛ የደመወዝ እርከን ጣሪያ የ12 በመቶ ማሻሻያ ተደርጎበታል፡፡
በኬንያ ዝቅተኛ የደመወዝ ጣሪያ 13 ሺህ 500 ሺልንግ ወይም 5 ሺህ 983 ብር ሲሆን በዚህ ላይ የ12 በመቶ ጭማሪ ሲደረግበት 15 ሺህ 120 የኬንያ ሽልንግ ወይም 6 ሺህ 701 ብር ሆኗል፡፡
ፕሬዝዳንት ኬንያታ የዝቅተኛ ደመወዝ ማሻሻያውን የወሰኑት በናይሮቢ ለ57ኛ ጊዜ በተከበረው የዓለም ላብ አደሮች ቀንን ምክንያት በማድረግ መሆኑን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል፡፡
ፕሬዝዳነቱ በንግግራቸው ላይ “ከዛሬ ከግንቦት 1 ቀን ጀምሮ በሰራተኞች ዝቅተኛ የደሞዝ እርከን ላይ የ12 በመቶ ጭማሪ መደረጉን አበስራለሁ“ ሲሉ ለበዓሉ ታዳሚዎች ተናግረዋል፡፡
“የግል አሰሪ ተቋማት ባንድ መንፈስ በጋራ እንስራ የሰራተኞቻችንን ደህንነት በጋራ መጠበቅ ትርፋችንን እናጋራ“ ሲሉም ፕሬዝዳንቱ አክለዋል፡፡
በፕሬዝዳንቱ አዲስ ውሳኔ መሰረት በኬንያ ላሉ ሰራተኞች የ1 ሺህ 620 ሽልንግ ተጨምሮላቸዋል፡፡
ኬንያ የዓለም ሰራተኞች ቀንን “ፖለቲካዊ ለውስጥ ለኢንዱስትሪ ሰላም፣ መረጋጋት እና ስራ ፈጠራ“ በሚል መሪ ሀሳብ አክብራለች፡፡
ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የደሞዝ እርከንን ለማስቀመጥ በሚያስችል ሂደት ላይ ነች መባሉ ይታወሳል፡፡