ፖለቲካ
ሶስት አደገኛ እስረኞች ከእስር ቤት ያመለጡባት ኬንያ የማረሚያ ቤት ዋና አዛዡን ከስልጣን አነሳች
ማረሚያ ቤት ዋና አዛዡን ከስልጣን ያነሱት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ናቸው
በኬንያ እስር ላይ የነበሩ ሶስት አደገኛ የሽብር አቀነባባሪዎች ከማረሚያ ቤት አምልጠዋል
የሽብር ወንጀል አቀነባባሪዎች ከእስር ቤት ያመለጣት ኬንያ የማረሚያ ቤት ዋና አዛዡን ከስልጣን አነሳች።
የኬንያው ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሀገሪቱ ማረሚያ ቤት ዋና አዛዥ የነበሩትን ብርጋዴር ጀነራል ዊስሊፍ ኦጋሎን ከስልጣን አንስተዋል።
- ፕሬዘዳንቱ በብርጋዴር ጀነራል ዊስሊፍ ኦጋሎ ቦታ በጡረታ ላይ የነበሩትን ኮማደር ጆን ኪባሶ ዋሪዮባን አዲሱ የኬንያ ማረሚያ ቤት ዋና አዛዥ አድርገው መሾማቸውን የኬንያ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል።
- በኡጋንዳ በደረሱ ሁለት የሽብር አደጋዎች 2 ሰዎች ሲሞቱ 33 ሰዎች ቆሰሉ
ፕሬዘዳንቱ ዋና አዛዡን ከስልጣን ያነሱት በሽብር ማቀነባበር ወንጀል ተጠርጥረው የእስር ጊዜያቸውን በመወጣት ላይ ያሉ ሶስት እስረኞች ከእስር ቤቱ ማምለጣቸውን ተከትሎ ነው።
ኬንያታ እርምጃውን የወሰዱት የኬንያ የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ ሽብርተኞቹ ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግለት ካሚቲ ማረሚያ ቤት ማምለጣቸው ብዙ ችግር ሊያመጣ ስለሚችል እርምጃ መወሰድ አለበት በሚል ማሳሰባቸውን ተከትሎ ነው።