ናይሮቢ ኬንያውያን አካባቢያቸውን ነቅተው እንዲጠብቁ አሳስባለች
ኬንያ፣ ትናንት በኡጋንዳ ሽብርተኞች ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ዜጎቿ ሁኔታዎችን በንቃት እንዲከታተሉ አሳሰበች፡፡
ናይሮቢ የትኛውንም ዐይነት የሽብር ጥቃት ለመከላከል በሚያስችል ተጠንቀቅ ላይ መሆኗን አስታውቃለች፡፡
በትናንቱ የካምፓላ ፍንዳታ አጥፍቶ ጠፊዎቹን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆስለዋል፡፡
ኬንያዊቷ የዓለም ሪከርድ ባለቤት አግነስ ቲሮፕ ሞታ ተገኘች
የሽብር ካሉት ጥቃት ጋር በተያያዘ ዝርዝር ማብራሪያን የሰጡት የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ ጥቃቱ በሽብርተኝነት በተፈረጀው አሊያንስ ፎር ዴሞክራሲ (ADF) ሶስት አጥፍቶ ጠፊዎች መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡
የኬንያ መንግስት ቃል አቀባይ የሃገራቸው የጸጥታ አካላት በተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውንና አጎራባች በሆኑ የድንበር አካባቢዎች ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኬንያውያን ነቅተው አካባቢቺውን እንዲጠብቅና አዳዲስ ነገሮችን ሲመለከቱ ለፖሊስ እንዲያስታውቁም ኮሎኔል ሳይረስ ኦጉና በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳስበዋል፡፡
ከአንድ ወር በፊት በካምፓላ ከተማ ባለ አንድ ሬስቶራንት ውስጥ በደረሰ ተመሳሳይ የሽብር አደጋ ሁለት ሰዎች የሞቱ ሲሆን ሀላፊነቱን አይኤስ አይ ኤስ ለድርጊቱ ሃላፊነት ወስዶ ነበር፡፡
በዚሁ ዓመት መስከረም ወር መጨረሻ ቀናት ላይ አንድ አጥፍቶ ጠፊ የሽብር ቡድን በፈጸመው ጥቃት እራሱን ገድሎ በርካቶችን ማቁሰሉ አይነጋም፡፡