በኡጋንዳ በደረሱ ሁለት የሽብር አደጋዎች 2 ሰዎች ሲሞቱ 33 ሰዎች ቆሰሉ
በኡጋንዳ ይህን መሰል የሽብር አደጋ ሲያጋጥም በሁለት ወራት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ነው
አደጋው የደረሰው በኡጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ሁለት ቦታዎች ነበር
በኡጋንዳ በደረሱ ሁለት የሽብር አደጋዎች 3 ሰዎች ሲሞቱ 33 ሰዎች ቆሰሉ፡፡
በኡጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ሁለት ቦታዎች በደረሱ የአጥፍቶ ጠፊዎች የሽብር ጥቃት ይ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሰዎች ሲሞቱ 33 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የከተማይቱ ፖሊስ አስታቋል፡፡
ኡጋንዳ ብረት ለበስ የውጊያ ተሽከርካሪዎችን አመረተች
በአደጋው ከቆሰሉት 33 ሰዎች ውስጥ አምስቱ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተገልጿል፡፡ የተጎጂዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ ይችላል፡፡
በካምፓላ ሁለት የገበያ ማዕከላት ላይ ደረሰ የተባለው ይህ የዛሬ ረፋድ የሽብር ጥቃት በአገሪቱ ፓርላማ መግቢያ አካባቢ ነው የተፈጸመው፡፡
የአገሪቱ ፖሊስ በበኩሉ አደጋው በሁለት የአገር ውስጥ የሽብር ቡድን አባላት አማካኝነት በተመሳሳይ ሰዓት በተለያዩ ቦታዎች ፍንዳታው መድረሱን ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት አስታውቋል፡፡
ኡጋንዳ በጦር አዛዧ ስርዓተ ቀብር ላይ ሊፈጸም የነበረ የቦምብ ጥቃት ማክሸፏን አስታወቀች
ይሁንና እስካሁን በሽብር ድርጊቱ ዙሪያ ሃላፊነት የወሰደ አካል እንደሌለ የተገለጸ ሲሆን የአገሪቱ ፖሊስ ድርጊቱን እየመረመርኩ ነው ብሏል፡፡
ከአንድ ወር በፊት በካምፓላ ከተማ ባለ አንድ ሬስቶራንት ውስጥ በደረሰ ተመሳሳይ የሽብር አደጋ ሁለት ሰዎች የሞቱ ሲሆን ሀላፊነቱን አይኤስ አይ ኤስ ለድርጊቱ ሃላፊነት ወስዶ ነበር፡፡
በዚሁ ዓመት መስከረም ወር መጨረሻ ቀናት ላይ አንድ አጥፍቶ ጠፊ የሽብር ቡድን በፈጸመው ጥቃት እራሱን ገድሎ በርካቶችን ማቁሰሉ አይነጋም፡፡