በኬንያዊቷ አትሌት አግነስ ቲሮፕ ግድያ የተጠረጠረው ባለቤቷ ፍርድ ቤት ቀረበ
የዓለም ሪከርድ ባለቤት አግነስ ቲሮፕ በሳለፍነው ረቡዕ በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ ነው ሞታ የተገኘችው
አትሌት አግነስ ቲሮፕ በስለት ተወግታ ህይወቷ ማለፉም ተነግሯል
በኬንያዊቷ አትሌት አግነስ ቲሮፕ ግድያ ተጠረጠረው ባለቤቷ በዛሬው እለት ፍርድ ቤት መቅረቡ ተሰምቷል።
ኢብራሂም የተባለው እና በብዛት ኢማኑኤል ሮቲች በሚል መጠሪያ የሚታወቀው በኬንያዊቷ አትሌት አግነስ ቲሮፕ ባለቤት ባሳለፍነው ሳምንት በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።
በአትሌት አግነስ ቲሮፕ ግድያ የተጠረጠረው ባለቤቷ ለረጅም ሰዓታት በፖሊስ ክትትል ከተደረገበት በኋላ በኬንያዋ ሞንባሳ ከተማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ የተታወሳል።
በአትሌት አግነስ ቲሮፕ ግድያ የተጠረጠረው ባለቤቷ ኢማኑኤል ሮቲች በዛሬው እለት በኬንያ ፍርድ ቤት መቅረቡም ነው የተነገረው።
ፖሊስ ተጠርጣው ላይ ምርመራ እንዳልጨረሰ ማሳወቁን ተከትሎም ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ ተጨማሪ የ20 ቀናት የምርመራ ጊዜ የፈቀደ ሲሆን፤ እስከዚያው ተጠርጣሪው በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲቆይም ውሳኔ አሳልፏል።
በተጨማሪም የአዕምሮ ጤና ምርመራ እንዲደረግበትም ነው የታዘዘው።
የ25 ዓመቷ የዓለም ሪከርድ ባለቤት አግነስ ቲሮፕ ባሳለፍነው ረቡዕ ነበር በምእራብ ኬንያ አይተን ከተማ ቢገኘው ቤቷ ውስጥ በስለት ተወግታ ሞታ መገኘቷ ይታወሳል።
በ2015ቱ የዓለም ሃገር አቋራጭ ሻምፒዮና ደምቀው ከታዩ አትሌቶች መካከል አንዷ የነበረችው ቲሮፕ በቅርቡ በተካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ኬንያን ወክለው ከነበሩ አትሌቶች መካከል አንዷ ነች።
ሲፋን ሃሰን ባሸነፈችው እና ሄለን ኦቢሪ ሁለተኛ ጉዳፍ ጸጋዬ ደግሞ ሶስተኛ ሆነው ባጠናቀቁት የ10 ሺ ሜትር ርቀት ላይ ብርቱ ፉክክርን በማድረግ በአራተኛነትም ነው ያጠናቀቀችው።
ባሳለፍነው ወርሃ መስከረም በጀርመን በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አዲስ ክብረ ወሰንን ለማስመዝገብም ችላ ነበረ።