ካሚኒ ሙስሊም ሀገራት ወደ እስራኤል የሚልኩትን ነዳጅ እና ምግብ እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል
የኢራቁ ሀይማኖታዊ መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒ ሙስሊም ሀገራት በእስራኤል ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ አሳስበዋል።
ካሚኒ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የምታደርገውን ድብደባ እንድታቆም ሙስሊም ሀገራት ወደ እስራኤል የሚልኩትን ነዳጅ እና ምግብ እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።
"በጋዛ እየተደረገ ያለው ድብደባ በአስቸኳይ መቆም አለበት... ምግብ እና ነጃድ ወደ ጽዮናዊ መንግስት የሚደርስበት መንገድ መዘጋት አለበት" ሲሉ ተናግረዋል ካሚኒ።
እስራኤል በጥቅምት ወር ድንበሯን በመጣስ 1400 ዜጎቿን የገደለባትን ጋዛን እያስተዳደረ ያለው እና በኢራን የሚደገፈውን ሀማስን ከምድረ ገጹ ለማጥፋት ዝታለች።
እስራኤል ጋዛን በሁሉም አቅጣጫ በመክበብ ከባድ የተባለ የአየር ድብደባ እያደረሰች ትገኛለች። የፍልስጤም ባለስልጣናት እንደገለጹት በእስራኤለ የአየር ጥቃት እስካሁን 8000 ሰዎች ተገድለዋል።
የኢራን ባለስልጣናት እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርጠውን ወረራ የማታቆም ከሆነ በቀጣናው በኢራን የሚደገፍ ጥምረት በእስራኤላ ላይ ጥቃት እንደሚከፍት ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።
በእስላሚዊ ሪፐብሊኳ ኢራን ሀማስን መደገፍ ከ1979 ጀምሮ ዋና የፖለቲካ ምሰሶ ተደርጎ ይወሰዳል።
የኢራኑ ከፍተኛ ባለስለጣን ካሚኒ እስራኤል "በፍልስጤማውን ላይ በምታደርሰው ወንጀል" አሜሪካ ተባባሪ ነች ሲሉ ከሰዋል።
የሙስሊሙ አለም በዚህ ወሳኝ ወቅት ከተጨቆኑት ፍልስጤማውያን ጋር የቆሙትን አይረሳም ሲሉ ተናግረዋል።
እስራኤል እየፈጸመች ካለው የአየር ጥቃት በተጨመሪ በጋዛ ውስጥ ገብታ ከሀማስ ጋር እየዋጋች እና ይዞታዋን እያሰፋች መሆኑን ገልጻለች።
ትናንት ጃባሊያ የስደተኞች ካምፕ ላይ ባደረሰችው ጥቃት የሀማስ ከፍተኛ አዛዥ መግደሏን አስታውቃለች። ነገርግን ሀማስ በካምፑ አዛዥ አልነበረም ሲል አስተባብሏል።
የጋዛ የጤና ባለስልጣናት በአየር ጥቃቱ 50 ንጹሃን ተገድለዋል ብለዋል።
እስራኤል በጋዛ ላይ እየወሰደች ያለውን ጥቃት አጠናክራ ቀጥላለች።