የኢራኑ መሪ ካሚኒ እስራኤል በሶሪያ ላደረሰችው የኢምባሲ ጥቃት "መቀጣት አለባት" አሉ
የኢምባሲው ጥቃት በባላንጣዎቹ እስራኤል እና ኢራን መካከል ያለው ውጥረት ከፍ አድርጎታል ተብሏል።
እስራኤል ሳታደርሰው አትቀርም በተባለው ጥቃት ሰባት ወታደራዊ አማካሪዎች መገደላቸውን ኢራን መግለጿ ይታወሳል
የኢራኑ መሪ ካሚኒ እስራኤል በሶሪያ ላደረሰችው የኢምባሲ ጥቃት "መቀጣት አለባት" አሉ።
የኢራኑ መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒ እስራኤል በሶሪያ በሚገኘው የኢራን ኢምባሲ ግቢ ውስጥ ላደረሰችው ጥቃት "መቀጣት አለባት" ሲሉ ተናገረዋል።
እስራኤል ሳታደርሰው አትቀርም በተባለው የሚያዝያ አንዱ ጥቃት ሰባት ወታደራዊ አማካሪዎች መገደላቸውን የገለጸችው ኢራን እስራኤል እንደምትበቀል ዝታለች።
የኢምባሲው ጥቃት በባላንጣዎቹ እስራኤል እና ኢራን መካከል ያለው ውጥረት ከፍ አድርጎታል ተብሏል።
ካሚኒ ረመዳን ፆም ማብቂያ ላይ ባሰሙት ንግግር "ሰይጣናዊው መንግስት ስህተት ስርቷል፤ መቀጣት አለበት። ይቀጣልም"ብለዋል።
እስራኤል ፈጽመዋለች በተባለው በዚህ ጥቃት ከተገደሉት ውስጥ ሁለት የኢራን ጀነራሎች እንደሚገኙበት ኢራን ማስታወቋ ይታወሳል።
የኢራንን ዛቻ የሰማችው እስራኤል ከኢራን ሊቃጣ የሚችል ማንኛውንም አይነት ጥቃት ለመመከት ዝግጁ መሆኗን በመከላከያ ሚኒስሯ ዩአብ ጋላንት በኩል ገልጻለች።
ከእስራኤል ጋር እየተወዋጉ ላሉት የሀማስ እና የሄዝቦላ ታጣቂዎች ድጋፍ በማድረግ ኢራንን የምትከሰው እስራኤል በዚህ ጥቃት ጉዳይ አስተያየት አልሰጠችም።
እስራኤል ቀደም ሲል በሶሪያ ውስጥ ያሉ የኢራን ወታደራዊ ኢላማዎችን እንደምትመታ ስትገልጽ የነበረ ቢሆኖም ኢምባሲ ታጠቃለች የሚል ግምት ግን አልነበረም።