የተፈጠረው ግጭት በአለም አቀፍ ደረጃ ድጋፍ ሲደረግለት የነበረው የሲቪል መንግስት ሽግግር ሂደት አደናቅፎታል
የሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ለ3ኛ ቀን በድብደባ እየተናወጠች ነው።
አሜሪካ ሁለቱ ተፋለሚ ወገኖች ግጭት እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርባለች።
ግጭቱ ወደ ሲቪል አስተዳደር ትሸጋገራለች የተባለችውን ሱዳን ወደለየለት አምባገነን ስርአት እንዳያሸጋግራት ተሰግቷል።
የሱዳን ዶክተሮች ማእከላዊ ኮሚቴ ባወጣው መረጃ መሰረት በሱዳን ጦርነቱ ባለፈው ቅዳሜ ከጀመረ በኋላ በትንሹ 97 ንፁሀን ዜጎች ሲሞቱ 365 ቆስለዋል።
መንግስት የሟቾችን ቁጥር ይፋ አላደረገም።
ከሰኞ መጀመሪያ ጀምሮ በካርቱም ለሁለት ሰዓታት ያህል የቦምብ ድብደባ እና የአየር ድብደባዎች ሲሰሙ የነበረ አሁንም የመድፍ ተኩስ እንደቀጠለ ነው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል ።
ግጭቱወደ ሌሎች የሱዳን አካባቢዎች ተዛምቷል፤ የኃይለኛው የፈጣን ድጋፍ ሃይሎች (RSF) ከሱዳን ጦር ጋር ሲጋጩ ባለፉት 10 አመታት የመደመሪያ ጊዜ ነው።
የሁለቱም ወገኖች መሪዎች በሱዳን የገዥው ምክር ቤት ውስጥ ሁለት ከፍተኛ ቦታዎችን ይዘዋል።
የተራዘመ የስልጣን ሽኩቻ ሱዳን የረዥም ጊዜ ገዢ የነበሩት ኦማር አልበሽር በህዝባዊ አመጽ ከስልጣን ከተወገዱ ከአራት አመታት በኋላ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ልትወድቅ የምትችልበትን ስጋት ከፍ አድርጎታል።
የተፈጠረው ግጭት በአለም አቀፍ ደረጃ ድጋፍ ሲደረግለት የነበረው የሲቪል መንግስት ሽግግር ሂደት አደናቅፎታል።
በሱዳን ጦር እና በጀነራል ሀምዳን ደጋሎ በሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል የተጀመረው ጦርነት እንደቀጠለ ሲሆን ቦታ ከመያዝ አንጻር እርስበእርሱ የሚጋጭ መግለጫ እያወጡ ይገኛሉ።