የ75 ዓመቱ ንጉስ ቻርልስ በጊዜየዊነት ህዝበዊ እንቅስቃሴ ያቆማሉ ተብሏል
የብሪታያ ንጉስ ቻርልስ 3ኛ በካንሰር ህመም መጠቃታቸውን በኪንግሃም ቤተ መንግስት አስታወቀ።
ንጉሱ የተገኘባቸው የካንሰር አይነት የትኛው እንደሆነ ባይገለጽም፤ የሽንት ቧንቧ ዕጢ ካንሰር (ፕሮስቴት) እንዳሆነ ግን ቤተ መንግስታቸው በመግለጫው አስታውቋል።
የ75 ዓመቱ ንጉስ ቻርልስ 3ኛ መደበኛ ህክምናቸውን ባሳለፍነው ሰኞ መጀመራቸው የተገለጸ ሲሆን፤ በዚሁ ጊዜም በጊዜየዊነት ህዝበዊ እንቅስቃሴ ያቆማሉ ተብሏል።
ንጉስ ቻርልስ ህክምናቸውን እየተከታተሉ መሆኑን እና በቅርቡ ወደ ህዝባዊ አገልግሎታቸው እንደሚመለሱም በኪንግሃም ቤተ መንግስት አስታውቋል።
ሆኖም ግን ካንሰራቸው ስላለበት ደረጃ በይፋ የተገለጸ ነገር የለም።
የ75 ዓመቱ ንጉስ ቻርልስ 3ኛ እናታቸው የንግስት ኤልሳቤት ዳግማዊ ህልፈትን ተከትሎ ነው 2014 መስከረም ወር ላይ የብሪታንያ ንጉስ ሆነው ተሾሙ።
ብሪታንያን ላለፉት 70 ዓመታት በንግስትነት ያገለገሉት ንግስት ኤልሳቤት ዳግማዊ በተወለዱ 96 ዓመታቸው በህመም ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
ይሄንን ተከትሎም የንግስቲቱ የበኩር ልጁ የሆኑት ቻርልስ 3ኛ የብሪታንያ ንጉስ ሆነው ተሹመዋል።