የብሪታንያ ንግስት ኤልሳቤጥ በ96 ዓመታቸው ማረፋቸው ይታወሳል
የንግስት ኤልሳቤት ዳግማዊ ህልፈትን ተከትሎ ልዑል ቻርልስ የብሪታንያ ንጉስ ሆነው ተሾሙ።
ብሪታንያን ላለፉት 70 ዓመታት በንግስትነት ያገለገሉት ንግስት ኤልሳቤት ዳግማዊ በተወለዱ 96 ዓመታቸው በህመም ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
ይሄንን ተከትሎም የንግስቲቱ የበኩር ልጁ የሆኑት የ73 ዓመቱ ልጃቸው ልዑል ቻርልስ የብሪታንያ ንጉስ ሆነው ተሹመዋል።
የንግስቲቱ የቀብር ስነ ስርዓት ከ17 ቀናት በኋላ ክብራቸውን በጠበቀ መንገድ እንደሚከናወን ተገልጿል።
የብሪታንያ ንጉስ ቻርልስ ሹመታቸውን ተከትሎ ከማንኛውም ፖለቲካዊ ውግንና ገለልተኛ ናቸው።
ንጉሱ የብሪታንያ ምልክት ተደርገው የሚወሰዱ ሲሆን የብሪታንያ ህግን በማጽደቅ ብቸኛው ሰው ናቸው።
ንጉሱ ከዚህ በተጨማሪም የብሪታንያን መሪ ሹመትን የሚያጸድቁ ሲሆን የሀገሪቱን ምክር ቤት በመክፈት የዓመት እቅዶችንም ያጸድቃሉ።
ንጉሱ በብሪታንያ የቀውስ ጊዜ ከተከሰተ እና መንግስቱ ያንን መቆጣጠር ካቃተው አዲስ መንግስት እንዲመሰረት የማድረግ ስልጣን አላቸው።
አዲሱ ንጉስ ቻርልስ እንግሊዝ ቤተክርስቲያን የበላይ ገዢ ሲሆኑ ጳጳሳትን እና የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን የመሾም ስልጣን አላቸው።