የብሪታንያ ንጉስ ቻርልስ በዓለ ሲመት ነገ በለንደን ይከበራል
የብሪታንያ ንጉስ ቻርልስ ነገ በቅኝ ግዛት የተያዙ በተለያዩ አህጉራት ያሉ ሀገራት መሪዎች፣ የሀገሪቱ ዜጎች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ባሉበት በዓለ ሲመታቸው ይከበራል።
ንጉስ ቻርልስ በዚህ በዓል ላይ የሚጓዙባቸው የወርቅ ቅብ ሰረገላዎች ይፋ ሆነዋል።
እነዚህ ሰረገላዎች አንዱ ንጉስ ቻርልስ እና ባለቤታቸው ካሚላ ከቤተመንግስት ወደ ዌስት ሚንስትር ቤተ ክርስቲያን የሚጓዙበት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከቤተ ክርስቲያን ወደ ቤተ መንግሥት ይመለሱበታል ተብሏል።
ሰረገላዎቹ በፈረንጆቹ 2014 አውስትራሊያ የንግስት ኤልዛቤዝ 60ኛ ዓመት የንግስና በዓልን ለማክበር በሚል የተሰሩ እንደሆኑ ተገልጿል።
የአነዚህ ሰረገላዎች በርና መስኮት በወርቅ አልማዝ እንቁ የተንቆጠቆጡም ናቸው ተብሏል።
በብሪታንያ የንጉሳዊ አስተዳድር ከተጀመረ 260 ዓመት ሞልቶታል የተባለ ሲሆን በንጉስ ዊሊያም አራተኛ በፈረንጆቹ ከ1830 ጀምሮ ሲከወን እንደኖረም ተገልጿል።
የብሪታንያ ንጉስ ቻርልስ በዓለ ሲመት ነገ በለንደን የሚከበር ሲሆን የአፍሪካ መሪዎች በዓሉን ለመታደም ለንደን ደርሰዋል።
በዚህ በዓል ላይ ለመታደም የቀድሞ የብሪታንያ ቅኝ ግዛት የነበሩ ሀገራት ወደ ለንደን አምርተዋል።
ከአፍሪካም የሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ፣ የዝምባብዌ ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናጋግዋ፣ የኢስዋትኒ ንጉስ ማስዋቲ፣ የማላዊ ፕሬዝዳንት ላዛሪስ ቻክዌራ፣ የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሀኪንዴ ሂቺልማ፣ የላይቤሪያው ጆርጅ ዊሀ እና ሌሎችን ለንደን ደርሰዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
በአውሮፓ ጉብኝት ወቅት የአፍሪካ መሪዎች ተገቢውን ክብር አያገኙም በሚል ከሰሞኑ አስተያየት የሰጡት የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ወደ ለንደን ይሂዱ ወይም ተወካይ ይላኩ እስካሁን አለመታወቁ ተገልጿል።