በርካታ የሩሲያ መኪና አምራቾች ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ፍላጎት እንዳላቸውም ተገልጿል
የሩሲያ ላዳ መኪናዎች ኢትዮጵያ ውስጥ መመረት ሊጀምሩ መሆኑ ተገለጸ።
በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ቻም ኡጋላ ከሩሲያው ታስ የዜና ኤጀንሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የሩሲያ ላዳ መኪናዎች በቅርቡ በኢትዮጵያ መመረት እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚረቱ የላዳ መኪናዎች ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ለአፍሪካ ገበያ የሚቀርቡ መሆኑንም አምባሳደሩ ተናግረዋል።
አምባሳደር ቻም ኡጋላ “አዳዲስ የላዳ መኪናዎችን በኢትዮጵያ እና በጉረቤት ሀገራት በቅርቡ ማየት እንጀምራልን፤ ምክንያቱ ደግሞ የላዳ አምራች ኩባንያ አስቶቫስ ከኢትዮጵያ ኩባንያ ጋር በስምምነት ደርሷል” ብለዋል።
በኢትዮጵያ የሚመረቱት የላዳ መኪናዎች ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ወደ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያን እና ሶማሊያ እንደሚላኩም አስታውቀዋል።
ላዳ መኪናዎች በኢትዮጵያ መመረት የሚጀምሩበት ጊዜ ቅርብ መሆኑንም አምባሳደር ቻም ኡጋላ ገልጸዋል።
ላዳኢትዮጵያ ውስጥ ምርት የመጀመር እርምጃው ኢትዮጵያ ለምንብሪክስን እንደተቀላቀለች የሚያሳይ ነው ያሉት አመረባሳደሩ፤ ዝቅተኛ የማምረቻ ወጪ እና እያደገ ላለው የአፍሪካ ገበያ ተደራሽነትን ለማስፈን ያስችላል ብለዋል።
ሌሎች የሩሲያ መኪና አምራች ኩባንያዎችም በኢትዮጵያ የመኪና መገጣጠም ዘርፍ ላይ ለመሰማራት ፍላጎት እያሳዩ መሆኑን አምባሳደሩ ጠቅመዋል ሲልም ታስ ዘግቧል።