ሞስኮ ም/ቤቱ የምዕራባዊያን የፖለቲካ መሳሪያ እንዳይሆን ፍላጎቷን ገልጻለች
ሞስኮ የዓለምን አቋም ይለያል ለተባለው የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት የአባልነት ምርጫ ለመወዳደር ፍላጎቷን አሳይታለች።
ሩሲያ ከተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባልነቷን አቋረጠች
ሩሲያ በዩክሬን ላይ የጀመረችውን ጦርነት ተከትሎ ከም/ቤቱ ባለፈው ሚያዝያ ተባራለች።
አሁን ላይ የሞስኮ ዲፕሎማቶች ሀገራቸውን ለሦስት ዓመታት ለሚቆየው አባልነት ዳግም ለማስመረጥ ቆርጠው መነሳታቸው ተነግሯል።
ቢቢሲ ሩሲያ ከተመድ አባላት ድጋፍ ለማሰባሰብ የበተነችውን ሰነድ መመልከቱን ዘግቧል።
የም/ቤቱ ምርጫ በሚቀጥለው ወር ይካሄዳል።
በቢቢሲ አየሁት ባለው ሰነድ ሰነድ ሩሲያ "ለሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ሁነኛ መፍትሄ" ለመውሰድ ቃል ገብታለች።
ከዚህ በተጨማሪም ሞስኮ ም/ቤቱ የአንድ ቡድን የፖለቲካ መሳሪያ እንዳይሆን የማስቆም ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች።
ዲፕሎማቶች ሩሲያ በዩክሬንና ሀገር ውስጥ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ለሚቀርብባት ክስ ዓለም አቀፋዊ አመኔታን ለማግኘት እየሞከረች ነው ብለዋል።
መቀመጫውን ጄኔቫ ያደረገው የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት 47 አባል ሀገራት ያሉት ሲሆን፤ እያንዳንዱ አባል ለሦስት ዓመታት ያገለግላል።
ሞስኮ በቀጣዩ ምርጫ ለመካከለኛውና ምስራቅ አውሮፓ የተያያዙ ሁለት መቀመጫዎችን ለመያዝ ከአልቤኒያና ቡልጋሪያ ጋር ትወዳደራለች።