የቡድን 7 ሀገራት በሩሲያ ዳይመንድ ላይ እግድ ሊጥሉ ነው
እገዳው በዚህ የከበረ ድንጋይ የሚካሄድን ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ግብይትን እንደሚያካትት ነው ተብሏል
የቡድን 7 ሀገራት የሩሲያን ዳይመንድ ወደ ሀገራቸው እንዳይገባ የማገድ እቅድን ከአንድ አመት በላይ ሲመክሩበት የነበረ ሲሆን በሚቀጥሉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ሊጸድቅ እንደሚችል የቤልጂየም ባለስልጣናት ተናግረዋል
የቡድን7 ሀገራት በሩሲያ ዳይመንድ ላይ እግድ ሊጥሉ መዘጋጀታቸው ተገልጿል።
እገዳው በዚህ የከበረ ድንጋይ የሚካሄድን ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ግብይትን እንደሚያካትት የሩሲያው አርፒ ዘግቧል።
የቡድን 7 ሀገራት የሩሲያን ዳይመንድ ወደ ሀገራቸው እንዳይገባ የማገድ እቅድን ከአንድ አመት በላይ ሲመክሩበት የነበረው ሲሆን በሚቀጥሉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ሊጸድቅ እንደሚችል የቤልጂየም ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የእግዱ ህግ ተግባራዊ የሚሆነው በፈረንጆቹ ጥር አንድ መሆኑም ተገልጿል።
የሩሲያ ዳይመንድ እንዳይገባ እግድ ለመጣል የወጣው እቅድ ከፍተኛ የከበሩ ድንጋይ አስገቢ ከሆኑት እንደ ቤልጀም ከመሳሰሉት ሀገራት ተቃውሞ ሲገጥመው ቆይቷል።
ቀደም ሲል የቤልጀም ባለስልጣናት የሩሲያን ዳይመንድ ለመከታተል የሚያስችል ስርአት ሳይኖር እግድ መጣል ገበያው ወደ ቻይና እና ህንድ እንዲያዘነብል ስለሚያደርግ ትርጉም አይኖረውም ብለውም ነበር።
4.5 ቢሊዮን ዶላር የሚገመተውን የሩሲያን የዲያመንድ ገበያ ለመቀነስ በማሰብ ባለፈው ግንቦት ወር የቡድን 7 አባል ሀገራት በሩሲያ በወጣ እና በተሰራ ዳይመንድ ላለመገበያየት ቃል ገብተው ነበር።
ይጣላል የተባለው እግድ ዳይመንዱ የወጣበትን ሀገር ለመለየት የሚያስችል አካላዊ ምርመራን ያካተተ ሲስተም ያስተዋውቃልም ተብሏል።
እስካሁን አሜሪካ እና እንግሊዝ የሩሲያ ዲያመንድ እንዳይገባ እግድ ጥለዋል።