በርካታ የአውሮፓ ኩባንያዎች በገበያ መጥፋት ምክንያት ለኪሳራ እየተዳረጉ ነው
ቅንጡ መኪና አምራቹ ላምቦርጊኒ የኤሌክትሪክ መኪኖችን እንደማያመርት ገለጸ፡፡
በተለምዶ ቅንጡ እና ውብ መኪኖችን በማምረት የሚታወቀው ላምቦርጊኒ ኩባንያ አሁን ላይ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለማምረት ዝግጁ እንዳልሆነ አስታውቋል፡፡
መቀመጫውን ጣልያን ያደረገው ይህ ኩባንያ የኤሌክትሪክ መኪኖችን የማያመርተው ገበያው የተረጋጋ አይደለም በሚል ነው፡፡
ውድ መኪኖችን በማምረት የሚታወቀው ይህ ኩባንያ እንዳለው ከሆነ ገዢዎች የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለመግዛት ያላቸው ፍላጎት ዝቅተኛ የሚባል ነው ብሏል፡፡
በዚህም ምክንያት ቅንጡ የኤሌክትሪክ መኪኖችን የሚያመርተው በ2029 እንደሆነ የኩባንያው ስራ አስፈጻሚ ስቴፋን ዊንክለማን ለዩሮ ኒውስ ተናግረዋል፡፡
ሌላኛው የጣልያኑ ቅንጡ መኪና አምራቹ ፌራሪ በበኩሉ በሚቀጥለው ዓመት የኤሌክትሪክ መኪኖችን ማምረት እጀምራለሁ ሲል አሳውቋል፡፡
አለም አቀፍ የመኪና አምራቾች እና የገበያ ድርሻቸው ምን ይመስላል?
አውሮፓ ህብረት ከ2035 ጀምሮ በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖች ሙሉ ለሙሉ እንዲቆም እቅድ መያዙን ተከትሎ በርካታ የአውሮፓ መኪና አምራች ኩባንያዎች ትኩረታቸውን ወደ ኤሌክትሪክ መኪኖች አዙረዋል፡፡
ይህን ተከትሎ ገዢዎች አሁንም የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለመግዛት ያላቸው ፍላጎት መቀነሱን ተከትሎ ኪሳራዎችን እያስመዘገቡ ናቸው፡፡
ግዙፉ ቮልስዋገንን ጨምሮ ሌሎች ኩባንያዎች ኪሳራ ያጋጠማቸው ሲሆን ሰራተኞቻቸውን እና የማምረቻ ፋብሪካዎችን እንደሚዘጉ አሳውቀዋል፡፡
የአውሮፓ ህብረት የነዳጅ መኪኖች ከ2035 ጀምሮ በአህጉሪቱ ሀገራት እንዳይነዱ ያሳለፈው ውሳኔ ተፈጻሚነትን በሚቀጥለው ዓመት እንደሚገመግም ማሳወቁ ይታወሳል፡፡