በብራዚል የተገነባው ትልቁ የክርስቶስ ሀውልት
የሀውልቱ ቁመት 48 ሜትር ሲሆን በሪዮ ዴ ጄኔሮ የሚገኘው ዝነኛው የክርስቶስ ሀውልትን በ5 ሜትር የሚበልጥ ነው
በብራዚል ደቡባዊ ክፍል ኢንካነታዶ ኮረብታማ ስፋራ የተገነባው አዲሱ ሀውልት ‘’ጠባቂው ክርስቶስ’’ የተሰኘ ስያሜ ተሰጥቶታል
ብራዚል በዓለም ትልቁን የክርስቶስ ሀውልት የገነባቸው ሲሆን ሲሆን ቁመቱም 43 ሜትር ነው ተብለዋል፡፡
የተገነባው የክርስቶስ ሀውልት፤ በሪዮ ዴ ጄኔሮ የሚገኘውን ባለ 38 ሜትር ቁመት ዝነኛው የክርስቶስ ሀውልትን 5 ሜትር የሚበልጥ ነው፡፡
በብራዚል ደቡባዊ ክፍል ኢንካነታዶ ኮረብታማ ስፋራ የተገነባው አዲሱ ሀውልት ‘’ጠባቂው ክርስቶስ’’ የተሰኘ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ ሀውልቱ ከፍታ ባለው ኮረብታማ ቦታ ተተክሎ ሪዮ ግራንዴ ዶሱል ከተማን ያያል ሲልም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የሀውልቱ የመጨረሻ ማስዋብ ስራዎች የሰራው ብራዚላዊው አርቲስት አዲሱን ሀውልት በተመለከተ “በጣም ስሜቴ ተነካ፤ በትክክል ልገልጸው የማልችለው ድቀን ስራ ነው" ሲል ያለውን ስሜት ለመገናኛ ብዙሃን ተናግሯል፡፡
የሀውልቱ ግንባታ የተጀመረው እንደፈረንጆቹ 2019 ሲሆን አብዛኛው ወጪው የተሸፈነው በአከባበው ከሚገኙ የንግድ ተቋማት መሆኑምን ታውቋል፡፡
ድንቅና የዓለማችን ትልቁ ሀውልት የመገንባቱ ሃሳብ፤ እንደፈረንጆቹ 2021 በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸው ያጡትን የከተማዋ ከንቲባ እንደነመበርም ነው የተገለጸው፡፡
ቀደም ሲል እንደፈረንጆቹ 1931 የተጠናቀቀውና በሪዮ የሚገኘው ሀውልት፤ ለግንባታው ኮንክሪት እና የሳሙና ድንጋይ ጥቅም ላይ የዋሉ ሲሆን ለግንባታው 9 አመታት ፈጅቶበታል፡፡