የዓለም ጤና ድርጅት የብራዚል ጤና ስርአት ኮሮና ቫይረስ እያሳደረ ያለውን ተጽእኖ መቋቋም መቻሉን ገልጿል
የዓለም ጤና ድርጅት የብራዚል ጤና ስርአት ኮሮና ቫይረስ እያሳደረ ያለውን ተጽእኖ መቋቋም መቻሉን ገልጿል
ብራዚል እስከ ትናንትና ድረስ 41828 በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች በማስመዝገብ ዩናይትድ ኪንግደምን(ዩኬ) በመብለጥ በሟቾች ቁጥር ከአለም ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት የሀገሪቱ የጤና ስርአት ኮሮና ቫይረስ እያሳደረ ያለውን ተጽእኖ መቋቋም መቻሉን ገልጿል፡፡
“ከመረጃው እንደምናየው የጤና ስርአቱ ያንያህል ከአቅሙ በላይ አልሆነም “ያሉት የድርጅቱ የድንገተኛ ጉዳይ ዳይሬክተር ማይክ ርያን ጥቂት የብራዚል ሆስቲታሎች የጽኑ ህሙማን አልጋዎችን 80 በመቶ በላይ መጠቀማቸውን ገልጸዋል፡፡
በብራዙል ብዙ ህዝብ ባለበት ቦታዎች ብዙ የኮሮና ተጠቂዎች አሉ፤ ነገርግን አንደአጠቃላይ ሲታይ ከአለም ሁለተኛ የጠቂዎች ቁጥር ባለበት ሀገር የጤና ስርአቱ መቋቋም ችሏል ብለዋል ርያን፡፡
የጤና ሚኒስቴር አርብ እለት ባወጣው ሪፖርት በብራዚል 828819 በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ሲኖሩ 25982 ሰዎቸ ደግሞ በአንድ ቀን ውስጥ ተይዘዋል፡፡ በዚሁ ሪፖርት 909 ሰዎች መሞታቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
ባለፈው ሀሙስ እልት የብራዚል ፕሬዘዳንት ቦልሶናሮ በሆስቲታል ውስጥ ያሉት የጽኑ ህሙማን አልጋዎች መያዛቸውን ወይንም አመያዛቸውን ለማወቅ ደጋፊዎቻቸው መላ ፈልገው እንዲያዩ አበረታትተዋል፤ ይህም ለብራዚል ፖሊስ ለደህንነት ሰዎች ለምርመራ የሚስፈልጋቸውን ተንቀሳቃሽ ምስል አንዲያገኙ ለማድረግ ነው፡፡
ሀሙስ እለት በሁለት ትላልቅ የብራዚል ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች ለሰአታት ሰልፍ ተሰልፈው ከሱፐርማርኬረት የሚስፈልጓቸውን እቃዎች ሲሸምቱ ተስተውለዋል፡፡በብራዚል የፍቅረኛሞች ቀን እለት ሱፐርማርኬት በሰዎቸ ተጥለቅልቀው ነበር፡፡
ኮሮና በብራዚል ይህን ያህል ሰው ከመቅጠፉ በፊት፤ የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ቦልሶናሮ ኮሮናን ቀለል አርጋችሁ እዩት ማለታቸውን በርካት ትችትን አስነስቶ ነበር፡፡