በ2023 በማር ንግድ በአለማቀፍ ደረጃ 9 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር እንደሚንቀሳቀስ ይጠበቃል
ከፈረንጆቹ 2000 ጀምሮ ባሉት ሁለት አስርት አመታት የማር ምርት በ40 በመቶ አድጓል።
በአለምአቀፍ ደረጃ በ2021 1 ነጥብ 77 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ማር መመረቱን የአለም አቀፉ የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) መረጃ ያመላክታል።
በአመቱ 500 ሺህ ቶን የሚጠጋ ማር የምታመርተው ቻይና ቀዳሚዋ ማር አምራች ሀገር ናት።
ከማር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማግኘት ግን ኒውዝላንድ ቤጂንግን ትቀድማለች።
ፋኦ ይፋ ያደረገውን የአለማችን ቀዳሚ ማር አምራች ሀገራት ዝርዝር ይመልከቱ፦