ኦሊጉነር ሶልሻየር ቀጣዩ የሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ?
ክለቡ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም እያደረገ ባለው ጥረት ሶልሻየር እና ዴቪድ አንቸሎቲ ከክለቡ ጋር ተያይዞ ስማቸው እየተነሳ ነው
ሶልሻየር ባለፉት 3 አመታት ከክለብ አሰልጣኝነት ውጭ ሆኖ ቆይቷል
ቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኦሊጉነር ሶልሻየር ቀጣዩ የሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡
የእንግሊዙ ክለብ የቀድሞውን አስልጣኝ ኤንዞ ማሬሳ ለመተካት እያደረገ ባለው ጥረት የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ ልጅ ዴቪድ አንቸሎቲ እና ኦሊጉነር ሶልሻየር ከክለቡ ጋር ስማቸው እየተነሳ ነው፡፡
ባለፉት 3 አመታት ከክለብ አሰልጣኝነት ውጭ ሆኖ የቆየው ሶልሻየር ከሌስተር ሀላፊዎች ጋር ንግግር መጀመሩ ነው የተነገረው፡፡
ሶልሻየር በማንቼስተር ዩናይትድ አሰልጣኝነት በቆየባቸው ሁለት የውድድር አመታት ከውጤት ጋር በተያያዘ ቅሬታ ቢቀርብበትም በሁለት አመቱ ውስጥ ክለቡ በሊጉ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡
ቀደም ሲል ከቱርኩ ክለብ ቤሺክታሽ ጋር ሰሙ ተያይዞ ሲነሳ የነበረው ሶልሻየር በእንግሊዝ ፕርሚየርሊግ መቆየትን ምርጫው ሊያደርግ ይችላል እየተባለ ነው፡፡
ከሌስተር አሰልጣኝነት ጋር በተያያዘ ስሙ አብሮ የሚነሳው ሌላኛው እጩ ዴቪድ አንቸሎቲ በማድሪድ ቤት ባለፉት አመታት ታክቲካል ጉዳዮችን በማማካር የአባቱ ቀኝ እጅ ሆኖ ቆይቷል፡፡
ከሌስተር በተጨማሪ የፈርንሳዩ ክለብ ሳይድሬሚስ ዲቪድ አንቸሎቲን ለመውሰድ ጥያቄ ቢያቀርብም የሻምፒዎንስሊግ አሸናፊው ክለብ ማድሪድ ዴቪድን ለተጨማሪ አንድ አመት በሳንቲያጎ በርናባው ማቆየት እንደሚፈልግ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
በክለብ ዋና አስልጣኝነት ሰርቶ የማያውቀው ዴቪድ በማድሪድ ቤት እያሳየ ያለው የታክቲካል ስልጠና ብቃት እና ከአባቱ የወሰደው የስልጠና ልምድ በእንግሊዝ ክለቦች ተፈላጊ እንዳደረገው ዘ ሰን ጋዜጣ አስነብቧል፡፡
የቀድሞ የቼልሲ አሰልጣኝ ግርሀም ፖተር ከሌስተር ጋር ስማቸው እየተነሳ ካሉ አሰልጣኞች መካከል አንዱ ሲሆን እስካሁን የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ባይደረስም ሌስተር ወደ ሶልሻየር ሊያደላ የሚችልበት አድል ሰፊ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡
ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ በመጣበት አመት በአስደናቂ ብቃት የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻለው ሌስተር በ2023/ 2024 የውድድር ዘመን ከሊጉ ድጋሚ ወርዶ ነበር፡፡
በ2024 /2025 ውድድር ዘመን ወደ ፕርሚየር ሊጉ የተመሰው ሌስተር በተያዘው አመት ከሚገኝበት የውጤት ቀውስ ለመውጣት ቀጣይ የሚሾመው አሰልጣኝ ወሳኝ ነው ተብሏል፡፡