የጣሊያኑ አትላንታ የጀርመኑን ባየርሊቨርኩሰን በማሸነፍ የመጀመሪያ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫውን አንስቷል
በፈረንጆቹ 1971 ጅማሮውን ያደረገው የዩሮፓ ሊግ ከሻምፒዮንስ ሊጉ ቀጥሎ በአውሮፓ ትልቁ ውድድር ነው።
የእንግሊዙ ቶተንሃም የመጀመሪያውን የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ ያነሳ ሲሆን፥ ከ1973 እስከ 2009 ኢንተርሚላን፣ ጁቬንቱስ እና ሊቨርፖል ሶስት ሶስት ጊዜ ሻምፒዮን ሆነዋል።
የስፔኑ ሲቪያ ሰባት ጊዜ የውድድሩን ዋንጫ በማንሳት የሚደርስበት አልተገኘም። ሲቪያ በ2014፣ 2015 እና 2016 በተከታታይ ዋንጫውን ማንሳቱም ይታወሳል።
የስፔን ክለቦች የዩሮፓ ሊግን በማንሳት ቀዳሚ ናቸው፤ አምስት ክለቦች 14 የሊጉን ዋንጫው አንስተዋል።
የጀርመኑን ባየርሊቨርኩሰን በማሸነፍ የ2024 ሻምፒዮን የሆነው አትላንታን ጨምሮ አምስት የጣሊያን ክለቦችም 10 የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን መውሰድ ችለዋል።
የእንግሊዝ አምስት ክለቦች ዘጠኝ፤ የጀርመን አምስት ክለቦች ደግሞ ሰባት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ማንሳታቸውንም የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር መረጃ ያመላክታል።
በዩሮፓ ሊግ የ53 አመት ታሪክ የ11 የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት 30 ክለቦች ሻምፒዮን መሆን ችለዋል።
የዩሮፓ ሊግን ደጋግመው የወሰዱትን ክለቦች ዝርዝር በቀጣዩ ምስል ይመልከቱ፦