የማንቸስተር ዩናይትድ አሠልጣኝ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬርን አሰናበተ
በፕሪምየር ሊጉ ማንቸስተር ዩናይትድ ከ12 ጨዋታዎች 17 ነጥብ በመሰብሰብ 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል
ሶልሻዬርና ማንቸስተር ዩናይትድ መለያየት ክለቡ ትናንት ከዋትፈርድ ጋር የነበረውን ጨዋታ መሸነፉ ነው
ማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር በይፋ አሰናበተ።
ክለቡ በይፋው ገጹ እንዳስታወቀው፤ ለአሰልጣኙ መሰናበት ዋነኛ ምክንያት ክለቡ ትናንት ከዋትፎርድ ጋር በነበረው ጨዋታ በመሸነፉ ነው።
“አሰልጣኝ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር ከዛሬ ጀምሮ ከኃላፊነቱ ተነስቷል” ነው ያለው ክለቡ።
በምትኩ ማይክል ካሪክ የዩናይትድ አሠልጣ ሆኖ በጊዜያዊነት መቀጠሩንም ጭምር አስታውቋል።
ለሶስት ዓመታት ያክል ማንቸስተር ዩናይትድን ያሰለጠኑት ሶልሻዬር በቅርብ ጊዜ ካደረጓቸው ሰባት የፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች በአምስቱ ሽንፈትን አስተናግዷል።
በዚህም በተለይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአሰልጣኙ ላይ “ሶልሻዬር ማንቸስተር የሚያክልን ትልቅ ክለብ የማሠልጠን ብቃት የላቸውም” የሚሉ ጫናዋች በከፍተኛ ደረጃ ሲደርሱና ሲስተዋሉ እንደነበር የሚታወስ ነው።
ከ12 ጨዋታዎች 17 ነጥብ በመሰብሰብ 7ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንቸስተር ዩናይትድ ፤በሶልሻዬር ምትክ በቋሚ አሠልጣኝነት ማንን ሊቀጥር እንዳሰብ እስካሁን ይፋ አላደረገም።
ኖርዌያዊው አሰልጣኝ በተጨዋችነት ዘመናቸው ለማንቸስተር ዩናይትድ ከፍተኛ አገልግሎት የሰጡ የፊት መስመር አጥቂ እንነበሩ የሚታወስ ነው።
ሶልሻዬር 67 ጊዜ ለብሄራዊ ቡዱናቸው ተሰልፈው የተጫወቱ አንጋፋ የእግር ኳስ ጠቢብ እንደነበሩም የሚታወቅ ነው።