በጄነራል ሀፍታር የሚመራው እና ትሪፖሊ ላይ የከተመው የሊቢያ ተፋላሚ ሀይሎች ተኩስ ለማቆም ተስማምተው ጣሱ፡፡
ሁለቱ ዋነኛ ተፋላሚዎች በጄነራል ከሊፋ ሀፍታር የሚመራው አብዛኛውን የሀገሪቱን ክፍል የተቆጣጠረው የሊቢያ ብሄራዊ ጦር እና ትሪፖሊ ላይ የከተመው ናሽናል አኮርድ ናቸው ተኩስ ለማቆም የተስማሙት፡፡
ተፋላሚዎቹ በሩሲያና ቱርክ ግፊት ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ተኩስ ያቁሙ እንጂ እስከመቼ እንደሚዘልቅ አልተገለጸም፡፡ ከዚህ በፊት መሰል የተኩስ አቁም ስምምነቶች በሰዓታት ልዩነት ተጥሰዋል ሮይተርስ እንደዘገበው፡፡
የተኩስ ማቆም ስምምነቱ በዋናነት ከፍተኛ ውጊያ ያለበትን ምዕራባዊውን የሀገሪቱን ክፍል የሚመለከት ቢሆንም አሁንም በዋና ከተማዋ ትሪፖሊ አካባቢ የተኩስ ድምጾች እንዳሉ እየተነገረ ነው፡፡
ምስራቅ ሊቢያን አጠቃልሎ ከመሀል እስከምዕራብ ዳርቻ አብዛኛውን የሀገሪቱን ክፍል በቁጥጥሩ ስር ያዋለው የጄነራል ከሊፋ ሀፍታር ጦር በአሁን ወቅት ትሪፖሊን ለመቆጣጠር መጠነ ሰፊ ጥቃት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በሀገሪቱ የነገሰውን ጦርነት እና አለመረጋጋት ተከትሎ ኢስላማዊ አክራሪ ታጣቂዎች እና ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች በሀገሪቱ እየመሸጉ ናቸው ተብሏል፡፡ ይሄም ከሀገሪቱ ጋር ሜዲተራኒያን ለሚያስተሳስራት አውሮፓ ተጨማሪ ራስ ምታት ሆኖባታል፡፡
ሙአማር ጋዳፊ እኤአ በ2011 ከተገደሉ ወዲህ ሀገሪቱ ከግጭት ነጻ ሆና አታውቅም፡፡
ሁለቱ የሀገሪቱ ተፋላሚዎች በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚደገፉ መሆናቸው ደግሞ ሀገሪቱን ከማረጋጋት ይልቅ ዳግማዊ ሶሪያ እንዳያደርጋት ተሰግቷል፡፡
በቅርቡ ቱርክ ናሽናል አኮርድን የሚረዳ ጦር ወደሀገሪቱ መላኳ ስጋቱን ይበልጥ አባብሶታል ዘገባዎች እንደሚያሳዩት፡፡ ቱርክ ጦሯን ከላከች በኋላም ቢሆን የጄነራል ሀፍታር ጦር ወደ ትሪፖሊ የሚያደርገውን ግስጋሴ አላቆመም፡፡ ጦሩ ባለፈው ሳምንት የሀገሪቱን ሶስተኛ ትልቅ ከተማ ሲርጥን መቆጣጠሩም ይታወቃል፡፡
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በኢስታንቡል ተገኛኝተው በሊቢያ ጉዳይ ከመከሩ በኋላ ተፋላሚዎቹ ተኩስ እንዲያቆሙ ቢያግባቡም ገና ስምምነት ከመደረሱ አንዱ ጦር ሌላውን ስምምነቱን በመጣስ ተኩስ ጀምሯል በሚል እርስ በእርስ መወነጃጀል ጀምረዋል፡፡