ይህ ሰው ህይወቱ ያለ ገንዘብ እና ቴክኖሎጂ ሰላማዊ እና ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል
ሕይወትን ያለ ገንዘብ እና ቴክኖሎጂ የሚኖረው ሰው
ማርክ ቦይል የተሰኘው እንግሊዛዊ በቢዝነስ ሙያ የመጀመሪያ ድግሪ ያለው ሲሆን በብሪስቶል ከተማ ጥሩ ደመወዝተኛ እንደነበር ይናገራል፡፡
ለዓመታት የነበረው እቅድ በታዋቂ ድርጅት ውስጥ በጥሩ ደመወዝ ተቀጥሮ ህይወትን ማጣጣም እንደነበር የሚናገረቀው ይህ ሰው በመጨረሻም የሕይወት ዘይቤው መቀየሩን ገልጿል፡፡
በፈረንጆቹ 2007 ላይ ካንድ ጓደኛው ጋር እየተመካከሩ ባለበት ወቅት ስለ ዓለም ችግሮች መወያየት ይጀምራሉ፡፡
በዓለማችን ላይ ላሉ ችግሮች ሁሉ መንስኤው ገንዘብ መሆኑን ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ማርክ ለሲኤንኤን ተናግሯል፡፡
በመቀጠልም “ዓለም እንዲለውጥ ከፈለክ አንት ቀድመህ ተለወጥ” የሚለው የታዋቂው ሕንዳዊ የነጻነት ታጋይ ማሃታማ ጋንዲ የፍልስፍና ሀሳብን መሰረት በማድረግ እኔ ያለ ገንዘብ ለመኖር ወሰንኩ ብሏል፡፡
ቦይል አክሎም ለዓለም ችግሮች ሁሉ ምንጩ የገንዘብ ፍላጎት ነው፣ ለገንዘብ ብዬ መኖርም የለብኝም የሚል አቋም ይዤ ውሳኔዬን እና ፍላጎቴን መተግበር ጀመርኩ ሲል ተናግሯል፤፡
ለፍላጎቶቻችን እና ተግባራችን መለያየት ዋናው ምክንያት ገንዘብ ነው የሚለው ቦይል ያለ ገንዘብ መኖሩን እንደጀመረ ገልጿል፡፡
የመጀመሪያው ስራዬም ጀልባዬን ሸጬ ወደ ገጠራማ አካባቢ በመሄድ ገንዘብ አልባ ህይወትን ጀመርኩ የሚለው ቦይል ለትንሽ ጊዜያት ህይወት ከብዶት እንደነበር አስታውቋል፡፡
ከዚያ በፊት የነበርኩበት ምቾት ገንዘብ አልባ ህይወቴ ላይ ችግር ፈጥሮብኝ ነበር የሚለው ይህ ሰው ቀስ በቀስ ግን ከተፈጥሮ ጋር እየተግባባ እና ህይወቱ እየተስተካከለ እንደመጣለት አክሏል፡፡
ግለሰቡ በ2010 ላይ ገንዘብ አልባ ህይወት የተሰኘ መጽሃፍ ጽፏል የተባለ ሲሆን በዚህ መጽሃፍ ስለ ገንዘብ ጉዳት፣ ስለ ህይወት ፍልስፍና እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ተዳሰውበታል ተብሏል፡፡
የአዕምሮ ጤናን በድምጽ የሚመረምር ቴክኖሎጂ በሚቀጥለው ወር ሙከራ ሊጀምር ነው
አሁን ከላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጥሩ ጓደኞች ማፍራቱን፣ ጭንቀት አልባ ህይወት እየመራ መሆኑን እና ህመም እሚባል አሞት እንደማያውቅም ተናግሯል፡፡
ምዕራቡ ዓለም የስነ ልቦና ድህነት ውስጥ መግባቱን የሚናገረው ማርክ ቦይል ጓደኝነት የሕይወት ትልቁ ዋስትና መሆኑን ተምሬያለውም ብሏል፡፡
ማርክ ቦይል በጊዜ ሂደት ከቴክኖሎጂ ጋር ያለውን ጥገኝነት በማላቀቅ ላይ መሆኑን የገለጸ ሲሆን ቴክኖሎጂዎች የሰው ልጆችን ህይወት ከማቅለል ይልቅ የበለጠ ያወሳስባሉ ብሎ እንደሚያምንም ገልጿል፡፡
ሁሉም ሰው ገንዘብ አልባ ህይወት መኖር እንደማይችል የሚናገረው ይህ ሰው ሰዎች ቀስ በቀስ ህይወታቸውን ከገንዘብ እና ቴክኖሎጂ ማላቀቅ ግን ይችላሉ ብሏል፡፡