“አውሮፓ ውስጥ ከባርሴሎና ውጪ ለሌላ ክለብ መጫወት ስላልፈለኩ ወደ አሜሪካ መጓዝን መርጫለሁ”- ሜሲ
አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ "ገንዘብ ብፈልግ ሳዑዲ አረቢያእሄድ ነበር" ሲልም ተናግሯል
ከፈረንሳዩ ፒ.ኤስ.ጂ ጋር የተለያየው ሊዮኔል ሜሲ ወደ አሜሪካው ክለብ ኢንተር ሚያሚ ለማምራት ወስኗል
አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ አሜሪካው ክለብ ኢንተር ሚያሚ ለመቀላቀል መወሰኑን አስታወቀ።
ከፈረንሳዩ ፒ.ኤስ.ጂ ጋር የተለያየው ሊዮኔል ሜሲትናንት ምሽት በሰጠው መግለጫ፤ ወደ ካታላኑ ክለብ ባርሴሎና እንደማይመለስ አስታውቋል።
ሊዮኔል ሜሲ አያይዞም ከአውሮፓ ክለቦች የዝውውር ጥያቄ የቀረበለት ቢሆንም አውሮፓ ውስጥ ከባርሴሎና ውጪ በሆነ ክለብ መጫወት ባለመፈለጉ አለመቀበሉን ተናግሯል።
ሜሲ አያይዞም አውሮፓ ውስጥ ከባርሴሎና ውጪ ለሌላ ክለብ መጫወት ባለመፈለጉ በቀጣይ ወደ አሜሪካው ክለብ ኢንተር ሚያሚ እንደሚያመራ ይፋ አድርጓል።
የሰባት ጊዜ የባላዶር አሸናፊው ሜሲ ቀጣይ ማረፊያው ኢንተር ሚያሚ መሆኑን ባሳወቀበት ወቅትም "ባርሴሎና መመለስ ብፈልግም የማይቻል ነው" ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።
የሰባት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ ወደ አሜሪካው ክለብ ኢንተር ሚያሚ ለማምራት የወሰነው ከገንዘብ ጋር በተያያዘ እንዳልሆነም አከሎ ገልጿል።
" ወደ አሜሪካ ለማቅናት ከውሳኔ የደረስኩት በገንዘብ ምክንያት አይደለም " የሚለው ሊዮኔል ሜሲ " የገንዘብ ጉዳይ ቢሆን ኖሮ ወደ ሳውዲ አረቢያ አቀና ነበር።"በማለት ተናግሯል።
አርጀንቲናዊው የአለም ሻምፒዮን ሊዮኔል ሜሲ በፈረንሳዩ የእግር ኳስ ክለብ ፓሪስ ሴንት ዤርሚያን ባሳለፍነው ቅዳሜ የመጨረሻ ጨዋታውን ማድረጉ ይታወሳል።
የፒ.ኤስ.ጂ አሰልጣኝ ክርስቶፈር ጋላታየር “በእግር ኳስ ታሪክ ምርጡን ተጫዋች የማሰልጠን እድል አግኝቼ ነበር” ማለታቸውን ይታወሳል።