አርሰናል ብራዚሊያዊውን ታዳጊ ሮኩን ለማስፈረም ከባርሴሎና ጋር ፉክክር ጀምራል ተብሏል
የሳውዲው አልሂላል ሊዮኔል ሜሲን በዓለም ክብረወሰን ዋጋ ለማስፈረም ጠየቀ።
የሳውዲ አረቢያ እግር ኳስ ሊግ ውድድር ፖርቹጋካዊውን ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ካስፈረመ በኋላ መነቃቃት ውስጥ ይገኛል።
ይህን ተከትሎም ሌላኛው የሳውዲ አረቢያ እግር ኳስ ክለብ አልሂላል አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲን ለማስፈረም ለፒኤስጂ ጥያቄ ማቅረቡን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
እንደ ዘገባው ከሆነ አልሂላል ለኒዮኔል ሜሲ በዓለም ታሪክ ከፍተኛውን የዝውውር ክፍያ ለመክፈል ዝግጁ ነው።
አል ሂላል ክለብ በተቀናቃኑ አልናስር የተወሰደበትን የበላይነት ለመመለስ ሊዮኔል ሜሲን የማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት አለው ተብሏል።
ወደ ሌላ እግር ኳስ ዜናዎች ስናልፍ ደግሞ የስፔኑ ሀያል ክለብ ሪያል ማድሪድ የቼልሲውን የመስመር ተመላላሽ ተጫዋች ሪክ ጀምስን የማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ተገልጿል።
ሌላኛው የስፔን ሀያል ክለብ ባርሴሎና የማንችስተር ሲቲውን ጀርመናዊ ኳስ አቀጣጣይ ኤካን ጉንዶሀንን ማስፈረም ይፈልጋል ቢባልም የክለቡ ወኪል ወሬው ሀሰት ነው ብሏል።
የእንግሊዙ አርሰናል ብራዚሊያዊውን ታዳጊ ሮኩን ለማስፈረም ከባርሴሎና ጋር ፉክክር መጀመሩ ሲገለጽ ቶትንሀም ሆስትስፐር ደግሞ የሀሪ ኪን ተተኪ አጥቂ ፍለጋ ላይ መሆኑ ተሰምቷል።
የብራይተኑ ኤቫን ፈርጉሰን ደግሞ በቶትንሀም የግዢ ራዳር ውስጥ መግባቱ ተገልጿል።
የቀድሞው የማንችስተር ተጫዋች ፓትሪክ ኤቭራ ሊድስ ዩናይትድን ለማሰልጠን ከክለቡ ጋር በንግግር ላይ ነው ተብሏል።
ቼልሲ ማሶን ማውንትን መግዛት የሚፈልግ ክለብ ካለ 70 ሚሊዮን ዩሮ በመክፈል መግዛት እንደሚችሉ ሲገልጽ ጋቦናዊ አጥቂው ፔር ኦቦሚያንግን ደግሞ ለኢንተር ሚላን ለመሸጥ በድርድር ላይ እንደሆነ ተገልጿል።