ስፖርት
ሊዮኔል ሜሲ ከሳዑዲ አረቢያው ክለብ በዓመት 320 ሚሊየን ፓውንድ ክፍያ ቀረበለት
የባርሴሎና የቡድን አጋሮቹ ሰርጂዮ ቡስኬት እና ጆርዲ አልባ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሊያቀኑ ይችላሉ ተብሏል
ሊዮኔል ሜሲ ቀጣዩን እርምጃ ለመወሰን እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ እንደሚቆይ ተነግሯል
አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ ከሳዑዲ አረቢያ አል-ሂላል በዓመት 320 ሚሊዮን ፓውንድ እንደቀረበለት ተነግሯል።
ክፍያው ለተጨዋቹ ከአንድ ወር በፊት ቢቀርብም ለመቀበል "አይቸኩልም" ተብሏል።
ሜሲ ከክለቡ ፒ.ኤስ.ጂ የሁለት ሳምንት እገዳ ቢኖርበትም የውድድር ዘመኑን ፍጻሜ በፈረንሳይ ሊግ ዋንጫ ማጠናቀቅ እንደሚፈልግ ተገልጿል።
ባርሴሎና እና ኢንተር ሚያሚ ተጨዋቹን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው የተባለ ሲሆን፤ ሆኖም ባርሳ የቀድሞ ኮከቡን ወደ ካምፕ ኑ ለመመለስ የገንዘብ ችግሩን መቅረፍ አለበት ተብሏል።
የስፔን ዜና ምንጮች ሜሲ በአል-ሂላል የቀድሞ የባርሴሎና ቡድን ጓዶቹ ሰርጂዮ ቡስኬትስ እና ጆርዲ አልባን ሊቀላቀል እንደሚችል ዘግበዋል።
ሜሲ ለሳዑዲ የቱሪዝም አምባሳደር ሲሆን በዓመት 25 ሚሊየን ፓውንድ ይከፈለዋል።
በክለቡ ያልተፈቀደ የተባለው የሪያድ ጉብኝት አርጀንቲናዊውን የእግር ኳስ ኮከቦ ከፓርክ ዴ ፕሪንስ መውጣቱን ያፋጥናል ሲል ደይሊ ሜል ዘግቧል።