በትናንቱ ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን እና የማርሴ ጨዋታ ሜሲና ምባፔ የየግል ወሰናቸውን አሻሽለዋል
ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን በእሁድ እለት በሊግ አንድ ከሜዳው ውጪ ተፎካካሪውን ማርሴን 3 ለ 0 በማሸነፍ በስምንት ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዡን በበላይነት ይዟል።
ኪሊያን ማባፔ እና ሊዮኔል ሜሲ ሦስቱንም የፓሪስ ሴንት ዠርሜይን ግቦች በመጣመር ያስቆጠሩ ሲሆን፤ በሂደቱም ግላዊ ደረጃዎችን አግኝተዋል።
ይህ ስኬት በህይወት ዘመኔ ስፈልገው የነበረው ነው- ሜሲ
ሜሲ በእግር ኳስ በህይወቱ 700ኛ የክለቡን ጎል ያስቆጠረ ሲሆን፤ ቁጥሩ በክርስቲያኖ ሮናልዶ ብቻ ተይዞ የነበረውን ወሰን የተዛመደ ነው ተብሏል።
ምባፔ ደግሞ ለክለቡ 200ኛ ጎል በማስቆጠር የፓሪስ ሴንት ዠርሜይን የጋራ ክብረ ወሰን ጎል አግቢ ሆኗል።
የፓሪስ ሴንት ዠርሜይን ዋና አሰልጣኝ ክሪስቶፍ ጋልቲየር ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "እሱ በዓለም ላይ ምርጥ አጥቂ ነው። ምክንያቱም እሱ በፍጥነት ስለሚጫወት እና የሚያደርገውን ሁሉ በፍጥነት ያደርጋል።"
በመጀመሪያው አጋማሽ ሜሲ እና ምባፔ ሁለቱም ጎል አስቆጥረውና አቀብለው ፒኤስጂ 2 ለ 0 እንዲመራ አድርገዋል።
ከእረፍት መልስ ምባፔ ሁለተኛው አጋማሽ ከተጀመረ በ10ኛው ደቂቃ ላይ የጨዋታውን ሦስተኛ ጎል አስቆጥሯል።