በጎርጎሮሲያዊያን ዘመን አቆጣጠር መሰረት አዲስ ዓመትን የማያከብሩ ሀገራት እነማን ናቸው?
ኢትዮጵያን ጨምሮ ጥቂት የዓለማችን ሀገራት የራሳቸው ዘመን አቆጣጠር አላቸው
አብዛኛው የዓለማችን ክፍል የጎርጎሮሲያዊያን ዘመን አቆጣጠርን የሚከተል ሲሆን አዲስ ዓመታቸውን በማክበር ላይ ናቸው
በጎርጎሮሲያዊያን ዘመን አቆጣጠር መሰረት አዲስ ዓመትን የማያከብሩ ሀገራት እነማን ናቸው?
አብዛኛው ዓለም የሚከተለው በጎርጎሮሲያዊያን ዘመን አቆጣጠር መሰረት የ2023 ዓመት ተጠናቆ አዲሱ 2024 ገብቷል፡፡
የአዲሱ ዓመት በዓል ዝግጅት በተለያዩ ሀገራት የተለያየ አከባበርን መሰረት አድርጎ እየተከበረ ሲሆን ጥቂት የዓለማችን ሀገራት ደግሞ እንደ መደበኛ የስራ ቀን ሆኖ እያለፈ ይገኛል፡፡
ለአብነትም ጥር ወር ላይ አዲ ዓመታቸውን ከማያከብሩ የዓለማችን ሀገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ስትሆን መስከረም አንድ ደግሞ አዲ ዓመት ወይም እንቁጣጣሽ የሙከበርበት እለት ነው፡፡
ልክ እንደ ኢትዮጵያ አሁን ላይ አዲስ ዓመትን የማታከብረው ሌላኛዋ ሀገር ቻይና ስትሆን ሀገሪቱ ሉናር የተሰኘ የራሷ ዘመን አቆጣጠር ሲኖራት የካቲት ላይ አዲስ ዓመቷን ታከብራለች፡፡
የነዳጅ ሀብት ባለጸጋዎቹ ሳውዲ አረቢያ እና ኢራን በጎርጎሮሲያዊያን ዘመን አቆጣጠር አዲ ዓመታቸውን ከማያከብሩ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ሲሆኑ የእስልምና ወይም ሂጅራ ዘመን አቆጣጠርን ትከታተላለች፡፡
የኢራን ዘመን አቆጣጠር ወይም አዲስ ዓመት ናወሩዝ የሚሰኝ ሲሆን የራሷ አቆጣጠር ካላቸው ጥቂት ዓለማችን ሀገራት መካከል አንዷ ናት፡፡
ሌላኛዋ የራሷ ዘመን አቆጣጠር ያላት ሀገር እስያዊቷ ሀገር ሕንድ ስትሆን ሚያዚያ ወር ላይ አዲስ ዓመቷን እንደምታከብር ተገልጿል፡፡
ታሚል የተሰኘው ይህ ዘመን አቆጣጠር ከሕንድ በተጨማሪም ማሌዢያ፣ ስሪላንካ እና ሲንጋፖርም ይህን የዘመን አቆጣጠር በመከተል ይታወቃሉ፡፡
ሲኦላል በመባል የሚታወቀው የኮሪያ ዘመን አቆጣጠር ስርዓት ሲሆን ሁለቱ ኮሪያዎች ሰሜን እና ደቡብ ኮሪያዎች ይከተሉታል፡፡
ሌላኛው የራሷ ዘመን አቆጣጠር ያላት ሀገር እስራኤል ስትሆን ሮሽ ሀሻናህ የተሰኘ ዘመን አቆጣጠር በመያዝ ከጥቂት የዓለማችን ሀገራት መካከል አንዷ ናት፡፡