አንድ ሰው አንድን አዲስ ዓመት በተለያዩ ሀገራት ላይ እንዴት ማክበር ይችላል?
የ2024 አዲስ ዓመትን በጃፓን ቶኪዮ ያከበሩ መንገደኞች ድጋሚ በአሜሪካም በማክበር ታሪካዊ ተብለዋል
የአሜሪካዋ ሳሞዓ ደሴት አዲሱን የ2024 ዓመት ዘግይተው ያከበሩ በሚል በታሪክ ተመዝግበዋል
አንድ ሰው አንድን አዲስ ዓመት በተለያዩ ሀገራት ላይ እንዴት ማክበር ይችላል?
አብዛኛው የዓለማችን ክፍል አዲሱን የፈረንጆቹ 2024 ዓመት በማክበር ላይ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ቀን ላይ ይገኛል፡፡
ይህን አዲስ ዓመት በጃፓን መዲና ቶኪዮ ያከበሩ መንገደኞች ወደ አሜሪካዋ ካሊፎርኒያ የነበረባቸውን ጉዞ አድርገዋል፡፡
እነዚህ መንገደኞችም አንድን አዲስ ዓመት በጃፓን እና በአሜሪካ ማክበር የቻሉ ሰዎች ሆነዋል፡፡
በራሳቸው ቀን አቆጣጠር አዲስ ዓመትን የሚያከብሩ ሀገራት እነማን ናቸው?
ክስተቱ የተፈጠረው የጃፓን እና የአሜሪካ ሰዓት አቆጣጠር ተመሳሳይ አለመሆኑን ተከትሎ ሲሆን መንገደኞቹ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ አዲሱን ዓመት ሲያከብሩ ያጋሯቸው ምስሎች መነጋገሪያ ሆነዋል፡፡
የጃፓኗ ቶኪዮ እና የአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ የ7 ሰዓታት ልዩነት መኖሩ አዲስ ዓመትን በጃፓን ያከበሩ መንገደኞችም ከሰዓታት በኋላ ወደ አሜሪካ የቀኑ መንገደኞች ይህንን አዲስ ዓመት ደግመው ለማክበር እድል ፈጥሮላቸዋል፡፡
አውስትራሊያ የ2024 አዲስ ዓመትን ከሁሉም የዓለማችን ሀገራት ቀድማ ያከበረች ሀገር ስትሆን የአሜሪካዋ ሳሞአ ደሴት ደግሞ ይህንኑ አዲስ ዓመት ከየትኛውም የዓለማችን አካባቢዎች ዘግይታ አክብራለች፡፡
50 ሺህ ህዝብ ብቻ የሚኖርባት ሳሞአ ደሴት በአሜሪካ እና አውስትራሊያ መካከል በደቡባዊ ፓሲፊክ ዊቂያኖስ ትገኛለች፡፡
በኮመን ዌልዝ ስር ያለችው ኪሪቲማቲ ደሴት ደግሞ አዲስ ዓመትን ቀድማ የምታከብር ሲሆን በሰሜናዊ ፓስፊክ ውቂያኖስ በኩል ለአሜሪካዋ ሳንፍራንሲስኮ ቅርብ የሆነች ደሴት ናት፡፡