በራሳቸው ቀን አቆጣጠር አዲስ ዓመትን የሚያከብሩ ሀገራት እነማን ናቸው?
ኢትዮጵያን ጨምሮ ጥቂት የዓለማችን ሀገራት ከምዕራባዊያን ዘመን በተለየ አዲስ ዓመታቸውን ያከብራሉ
ኢትዮጵያ፣ ኢራን፣ ቻይና፣ ሰሜን ኮሪያ እና ሌሎችም የራሳቸው ዘመን መቁጠሪያ ስርዓት አላቸው
ኢትዮጵያውያን በዛሬው እለት አዲሱን ዓመታቸውን በዛሬው እለት በማክበር ላይ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ጥቂት የዓለማችን ሀገራት ከምዕራባዊያን ዘመን በተለየ አዲስ ዓመታቸውን ያከብራሉ።
በዓለማችን 216 ሀገራት ያሉ ሲሆን 195ቱ በተመድ እውቅና የተሰጣቸው ሀገራት ናቸው።
ከነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ሀገራት አዲስ ዓመታቸውን በግሪጎሪያን ዘመን አቆጣጠር መሰረት ጥር አንድ ላይ የሚያከብሩ ናቸው።
- አባ ፍራንቸስኮስ መጪውን የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በማስመልከት መልዕክት አስተላለፉ
- ፓትርያርኩ በአዲሱ ዓመት የመሳሪያ አፈሙዞች በሙሉ ወደ መጋዝን መግባት እንዳለባቸው አሳሰቡ
ይሁንና ኢትዮጵያን ጨምሮ ጥቂት የዓለም ሀገራት በራሳቸው የቀን መቁጠሪያ የሚመሩ ሲሆን አዲስ ዓመታቸውንም በራሳቸው ባህል እና ወግ መሰረት ያከብራሉ።
የመካከለኛው ምስራቋ ኢራን በዓለም ላይ የራሳቸው የቀን አቆጣጠር ስርዓት እና አዲስ ዓመታቸው ከሚያከብሩ ሀገራት መካከል አንዷ ናት።
ኢራን ጸሀይን ወይም የሂጅራ ዘመን አቆጣጠርን መሰረት ያደረገ ስርዓት ያላት ሲሆን አዲስ ዓመትን ሁሌ መጋቢት ወር ላይ ታከብራለች።
ሌላኛዋ የራሷ ዘመን አቆጣጠር ስርዓት ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ደግሞ ቻይና ስትሆን ሉናር የተሰኘ ዘመን አቆጣጠር ስርዓትን ትከተላለች።
የቻይና አዲስ ዓመት የሚከበርበት ወር በየ አራት ዓመቱ የሚቀያየር ሲሆን አዲስ ዓመቱ የካቲት ወር ላይ ይከበራል።
ሩቅ ምስራቋ ሕንድ በራሷ የቀን መቁጠሪያ ስርዓት የምትመራ ሀገር ስትሆን ሚያዝያ ወር ደግሞ አዲስ ዓመቷን የምታከብርበት ወር ነው።
በየዓመቱ ጥቅምት ወር ላይ አዲስ ዓመቷን አሀዱ ብላ የምትጀምረው ሌላኛዋ ሀገር ደግሞ እስራኤል ስትሆን የሂብሪው ዘመን አቆጣጠርን ትከተላለች።
ከምዕራባዊያን ጋር ግጭት ውስጥ ያለችው ሰሜን ኮሪያም ሶላል የተሰኘ የራሷን የዘመን አቆጣጠር ስርዓትን የምትከተል ሲሆን አዲስ ዓመቷን የካቲት ወር ላይ ታከብራለች።
የእኛዋ ኢትዮጵያም በዓለም ላይ የራሷ ዘመን አቆጣጠር ስርዓት ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ሁሌ መስከረም ላይ አዲስ ዓመትን እንቁጣጣሽ በሚል መጠሪያ ታከብራለች።