መንታ በብዛት የሚወለዱባቸው የዓለማችን ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
አፍሪካ በዓለማችን መንታ የሚወለድባት አህጉር ተብላለች
የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ከሌሎች ሀገራት አንጻር መንታ ለመውለድ የበለጠ ተጋላጭ እንደሆኑ ተገልጿል
መንታ በብዛት የሚወለዱባቸው የዓለማችን ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ መንታ የሚወለደው በዘር፣ ከእርግዝና በፊት በሚወሰዱ መድሃኒቶች ድጋፍ፣በቁመት፣ በእናቶች እድሜ እና ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ነው፡፡
እንደ ቢዝነስ ኢንሳይደር ዘገባ ከሆነ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የበለጠ መንታ የሚወለድባቸው ሲሆን አፍሪካ ደግሞ የመንታዎች አህጉር ተብላለች፡፡
የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት በአፍሪካ ብዙ መንታዎች ከሚወለድባቸው ሀገራት መካከል ዋናው ሲሆን ቤኒን ደግሞ ቀዳሚዋ ዓለማችን ሀገር ነች፡፡
በቤኒን ከአንድ ሺህ እናቶች ውስጥ 28ቱ መንታ ይወልዳሉ ተብሏል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ መንታ የመውለድ ምጣኔ ከአንድ ሺህ ውልደት ውስጥ 13ቱ መንታ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው፡፡
ከቤኒን በመቀጠል ናይጀሪያ፣ ኮትዲቯር፣ ሕንድ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ፣ ዩክሬን እና ሌሎችም ሀገራት መንታዎች በብዛት ከሚወለድባቸው ሀገራት መካከል ናቸው፡፡