በጣሊያን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ኤየርፖርቶች ላይ ለተፈጸመው የሳይበር ጥቃት የሩሲያ ደጋፊ መረጃ መንታፊ ኃላፊነት ወሰደ
"ለሩሲያ ጥላቻ የሳይበር ምላሽ ያስፈልገዋል" ያለው የሩሲያ ደጋፊ ቡድን ኖኔም057(16) በቴሌግራም ገጹ ኃላፊነቱን እወስዳለሁ ብሏል
መረጃ መንታፊ ቡድኑ የውጭ ጉዳይ እና ሁለት ኤየርፖርቶችን ጨምሮ ጣሊያን ውስጥ 10 ድረ ገጾችን ኢላማ በማድረግ በጊዜያዊነት ስራ እንዲያቆሙ ማድረጉ ተገልጿል
በጣሊያን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ኤየርፖርቶች ላይ ለተፈጸመው የሳይበር ጥቃት የሩሲያ ደጋፊ መረጃ መንታፊ ኃላፊነት ወስዷል።
መረጃ መንታፊ ቡድኑ በትናንትናው እለት የውጭ ጉዳይ እና ሁለት ኤየርፖርቶችን ጨምሮ ጣሊያን ውስጥ 10 ድረ ገጾችን ኢላማ በማድረግ በጊዜያዊነት ስራ እንዲያቆሙ ማድረጋቸውን የሀገሪቱ የሳይበር ሴኩሪቲ ኤጀንሲ አስታውቋል።
"ለሩሲያ ጥላቻ የሳይበር ምላሽ ያስፈልገዋል" ያለው የሩሲያ ደጋፊ ቡድን ኖኔም057(16) በቴሌግራም ገጹ ኃላፊነቱን እወስዳለሁ ብሏል።
የጣሊያን ሳይበር ሴኩሪቲ ኤጀንሲ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት ጥቃቱ ከሩሲያ ደጋፊ ቡድን ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚገመት ነው።
መረጃ መንታፊዎች ሲስተሙን ከጥቅም ውጭ ለማድረግ ከፍተኛ መረጃ ወደ ትራፊኩ ይለቃሉ።
ቃል አቀባዩ ኤጀንሲው ጥቃት ለደረሰባቸው ተቋማት እና ኩባንያዎች ፈጣን ድጋፍ ማድረጉን እና ጥቃቱ ያደረሰውን ችግር ከሁለት ሰአታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ውስጥ መፍታት መቻሉን ገልጿል። የሳይበር ጥቃቱ በሚላኑ ሊኔት እና በማልፔንሳ ኤየርፖሮቶች የበረራ መስተጓጎል አለማድረሱን የሚቆጣጠራቸው ኩባንያ ኤስኢኤ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ አክሎም እንደገለጸው ድረ -ገጾቹ ከጥቅም ውጭ የነበሩ ቢሆንም የሞባይል መተግበሪያዎቹ ይሰሩ ነበር።