ፖለቲካ
በአውሮፕላን አደጋ የሞቱ የዓለም ሀገራት መሪዎች እነማን ናቸው?
ኢራንን ጨምሮ ሩዋንዳ ማላዊ እና ሞዛምቢክ ፓኪስታን መሪዎቻቸውን በአውሮፕላን አደጋ ካጡ ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው
በአንዳንድ ሀገራት የመሪዎች በአደጋ መሞትን ከፖለቲካ ጋር በማገናኘት ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንዲገቡ ምክንያት ሆነዋል
በአውሮፕላን አደጋ የሞቱ የዓለም ሀገራት መሪዎች እነማን ናቸው?
ባሳለፍነው እሁድ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ሬይሲን ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ መሪዎች በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡
የአውሮፕላን አደጋ በተለይም የሀገራት መሪዎችን ያሳፈሩ በረራዎች በከፍተኛ ጥንቃቄ የሚደረጉ ቢሆንም አልፎ አልፎ አደጋዎች አጋጥመው መሪዎች ለሞት ይዳረጋሉ፡፡
ከአፍሪካ ሩዋንዳ፣ ማላዊ፣ ሞዛምቢክ እና ቡሩንዲ በተለያዩ ጊዜያት ባጋጠሙ አደጋዎች የሀገራት መሪዎች ለሞት ተዳርገዋል፡፡
ከ32 ዓመት በፊት በሩዋንዳ ያጋጠመው የአውሮፕላን አደጋ በዓለማችን በዘግናኝነቱ ከሚታወሱ የእርስ በርስ ጦርነቶች መካከል አንዱ እንዲሆን ምክንት ሆኗል፡፡
ፕሬዝዳንት ጁቬናል ሀቢያሪማናን እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትን የጫነች አውሮፕላን መመታቷን ተከትሎ በተፈጠረው ክስተት በሩዋንዳ በተከሰተው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት 800 ሺህ ዜጎች ተገድለዋል፡፡
ፖላንድ፣ ሶሪያ እና ፓኪስታንም መሪዎቻቸውን የጫኑ አውሮፕላን ባጋጠማቸው አደጋዎች መሪዎች ተገድለዋል፡፡