አሜሪካ የኢራኑን ፕሬዝዳንት ህይወት ለቀጠፈው የሄሊኮፕተር አደጋ ለምን ድጋፍ ማቅረብ ተሳናት?
አሜሪካ የሄሌኮፕተር አደጋውን ተከትሎ “ከኢራን የድጋፍ ጥያቄ ቀርቦልኝ ነበር” ብላለች
አሜሪካ “በሄሌኮፕተር አደጋው ውስጥ እጇ የለበትም” በማለት አስታውቃለች
አሜሪካ በኢራን በደረሰው እና የፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲን ህይወት ለነጠቀው የሄሊኮፕተር አደጋ ልምን ድጋፍ ማቅረብ እንደተሳናት ገልጻለች።
የኢራኑን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲን ጨምሮ ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናትን ያሳፈረች ሄሊኮፕተር ላይ እሁድ አመሻሹን አደጋ መድረሱ ይታወቃል።
አደጋውን ተከትሎም ፕሬዝዳንቱን አሳፍራ ስትጓጓ የነበረችው አሜሪካ ሰራሽ ሄሊኮፕተር ሙሉ በሙሉ በእሳት መውደሟንም ነው የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ያስታወቁት።
ይህንን ተከትሎም የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚራብዶላሂያን ጨምሮ ሌሎቸም ከፍተኛ ባለስልጣናት አበደጋው ህይወታቸው ማለፉ ይታወቃል።
ሩሲያ እና ቱርክን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ለኢራን ድጋፍ የሚያደርጉ ቡድኖችን በመላክ አጋርነታቸውን ቢያሳዩም አሜሪካ ግን እካሁን በጉዳዩ ዙሪያ ዝምታን መርጣ ቆይታለች።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙሪያ ትናንት በሰጠው መግለጫ፤ “በሎጂስቲክስ ምክንያት የኢራንን የእርዳታ ጥያቄ ለመቀበል አልቻለም” በሏል።
"ከኢራን መንግስት እርዳታ ጥያቄ ቀርቦልን ነበር” ያሉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር “በዚህ አይነት ሁኔታ የውጭ መንግስት ለሚቀርብልን ማንኛውንም ጥያቄ ምላሽ እንደምንሰጥ ግልፅ አድርገንላቸው ነበር” ብለዋል።
“በአብዛኛው በሎጂስቲክስ ምክንያት ከኢራን መንግስት ለቀረበልን ጥያቄ እርዳታ ልንሰጥ አልቻልንም” ሲሉም ሚለር ተናግሯል።
ኢራን በአሜሪካ የተሰራው ቤል 212 ሄሊኮፕተር በአዘርባጃን ድንበር አቅራቢያ ባሉ ተራሮች ላይ ላይ መከስከሱን ተከትሎ መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን ምንም አይነት ይፋዊ መግለጫ አልሰጠችም።
ከዚሁ ጋር በተያያዘም ኢራን አሜሪካን እና የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ኦሊይድ ኦስቲንን ተጠያቂ ልታደርግ ትችል ይሆናል በሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ቃል አቀባዩ፤ ከዚህ አደጋ ጋር በተያያዘ ዩናይትድ ስቴትስ ምንም ድርሻ የላትም ብለዋል።
ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር አከልውም “ምክንያቱ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አልችልም” ሲሉ ተናግረዋል።