ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ የነበረው የቻይናው ሮኬት ስብርባሪ ህንድ ወቅያኖስ ላይ አረፈ
የቻይናው ሎንግ ማርች ቢ ሮኬት ስብርባሪ በኮትዲቯር አርፎ መጠነኛ ጉዳት አስከትሎ የነበረ መሆኑ ይታወሳል
የአሜሪካው የስፔስ ተቆጣጣሪ በትናንትናው እለት ምሽት የሮኬቱ ስብርባሪ ወደ ህንድ ውቅያኖስ ገብቷል ብሏል
ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ የነበረው የቻይና ሮኬት ስብርባሪ በትናንትናው እለት በህንድ ውቅያኖስ ላይ አርፏል፡፡
ነገርግን የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ማእከል ናሳ ቻይና የሮኩቱ ስብርባሪ የት ሊያርፍ እንደሚችል ለመገመት የሚያስችል ትክክለኛ መረጃ አላጋራቸውም ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ከቁጥጥር ውጭ የሆነው የቻይና ሮኬት አካል በአፍሪከ፣ አሜሪካ ወይም ደቡብ ኢሲያ ሀገራት ሊወድቅ ይችላል የሚል ግምት ተሰጥቶ ነበር፡፡
ከቁጥጥር ውጭ የሆነችው የቻይና ‘Long March-5B’ ሮኬት አካል በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ምድር እየተምዘገዘገች መሆኑ በረካቶች ዘንድ ስጋትን መፍጠሩን የአሜሪካው ኤሮስፔስ ኮርፖሬሽን ገልጾ ነበር፡፡
የአሜሪካው የስፔስ ተቆጣጣሪ በትናንትናው እለት ምሽት የሮኬቱ ስብርባሪ ወደ ህንድ ውቅያኖስ ገብቷል ብሏል፡፡
የናሳ አስተዳዳሪ ቢል ኔልሰን ሁሉም ሮኬት ወደ ጠፍር የሚያመጥቁ ሀገራት ትክክለኛ አሰራርን መከተልና እና ችግር ሲያጋጥም ደግሞ ስብርባሪው የት ሊያርፍ እንደሚችል ለመገመት የሚያስችል ትክክለኛ መረጃ ማጋራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡
በማሌዥያ የማህራዊ ሚዲያ ተቃሚዎች የሮኬት ስብርባሪ የሚመስል ተንቀሳቃሽ ምስል መልቀቃቻን ሮተርስ ዘግቧል፡፡
የኤሮስፔስ ኮርጆሬሽን ቻይና 22 ነጥብ 5 ቶን ክብደት ያለውን የሮኬት ስብርባሪ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ እንዲያርፍ ማድረግ ግዴለሽነት ነው ሲል ተችቷል፡፡ በዚህ ሳምንታ ቻይና የሮኬቱን ስብርባሪ እየተከታተለች መሆኑን እና ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት ትንሽ እንደሚሆን ገልጻ ነበር፡፡
ቻይና፤ ለአዲሱ የቻይና የጠፈር ማእከል የላብራቶሪ መገልገያ የያዘውን ሮኬት የተኮሰችው በፈረንጆቹ ሀምሌ 24 ነበር፡፡
በፈረንጆቹ 2020 የነበረው የቻይናው ሎንግ ማርች ቢ ሮኩት ስብርባሪ በኮትዲቯር አፍሮ መጠነኛ ጉዳት አስከትሎ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡