ዘሌንስኪ፤ የሮኬት ጥቃቱ ሩሲያ “የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ለማዋረድ” ያደረገችው ሙከራ ነው ብለውታል
የዩክሬኗ መዲና ኪቭ በሮኬት ተመታች፡፡
ኪቭ፤ በሮኬት የተመታቸው በሞስኮ ከቪላድሚር ፑቱን ጋር ቆይታ ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ወደ ዩክሬን አቅንተው ኪቭን ጨምሮ በሩሲያ ኃይሎች ከፍተኛ የስብዓዊ መብቶች ጥሰትና የጦር ወንጀል ወንጀል ተፈጽሞባታል የተባለቸው የቡቻ ከተማን እየጎበኙ በነበሩበት ወቅት ነው፡፡
የሮኬት ጥቃቱ ሩሲያ ሰሞኑን በደቡብ እና ምስራቅ ዩክሬን ዩክሬን የጀመረችው መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ አንዱ አካል ነው ተብሏል፡፡
ትናንት ማምሻው በደረሰው የሮኬት ጥቃት ቢያንስ ሶስት ሰዎች ሳይቆስሉ እንዳልቀሩም ነው ፍራንስ 24 የዘገበው፡፡ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ "በሼቭቼንኮቭስኪ አውራጃ ውስጥ ሁለት ጥቃቶች" እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡
ከጉቴሬዝ ጋር የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ ሳቪያኖ በበኩላቸው “የጦርነት ቀጠና ነው፣ ነገር ግን በአጠገባችን መከሰቱ አስደንጋጭ ነው” በልዑካን ቡድኑ ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ በመጠቆም፡፡
የፋሲካ በዓልን በማስመልከት በዩክሬን የተኩስ አቁም እንዲደረግ ተመድ ጠየቀ
ዜሌንስኪ፤ ከጉቴሬዝ ጋር ካደረጉት ውይይት በኋላ የተከሰቱት ጥቃቶች፤ ሩሲያ “የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን እና ድርጅቱ የሚወክለውን ሁሉን የማዋረድ ሙከራ” ሲሉ ድርጊቱን አውግዘውታል፡፡
የሮኬት ጥቃቱን በተመለከተ የሩሲያ ጦር ቃል አቀባይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ፤ የሞስኮ ጦር በ38 ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ የአየር ድብደባ እንደፈጸመ ከመናገር ውጭ በኪቭ ዙሪያ ያሉት ነገር የለም፡፡
ሩሲያ ልክ ጉቴሬ እና የቡልጋሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ክሪል ፔትኮቭ ለጉብኝት ኪቭ በደረሱበት ወቅት ከተማዋን በክሩዝ ሚሳዔል መደብደቧን የገለጹት የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሜትሮ ኩሌባ ሩሲያ ለዩክሬን ለአውሮፓም ሆነ ለዐለም ያላትን እይታ ያሳየችበት አረመኔያዊ ድርጊት ነው ኮንነውታል፡፡
የሩሲያ ጦር ወደ ኪቭ መገስገሱን አቁሞ በምስራቃዊ የሃገሪቱ አካባቢዎች ምዕራፍ ሁለት ያለውን አዲስ ዘመቻ ከፍቷል፡፡ የሩሲያ ፓርላማ (ዱማ) ከዩክሬን ተገንጥሎ በሪፐብሊክነት ለመመስረቱ እውቅና በሰጠው ምስራቃዊ ዶንባስ ግዛት ውስጥም እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ሆኖም በዘመቻው ውጤታማነት ላይ ጥያቄዎች በመነሳት ላይ ናቸው፡፡
ጦሩ ከኪቭ ካፈገፈገ በኋላ በቡቻ በደርዘን የሚቆጠሩ ንጹሃን ሞተው እንደተገኙ ይነገራል፡፡ ጅምላ ጭፍጨፋ ተፈጽሟል የዩክሬን አቃቤ ህግም በወንጀሉ ጠርጥረያቸዋለሁ ባላቸው 10 የሩሲያ ወታደሮች ላይ ምርመራ መጀመሩንና ከ8 ሺ በላይ የጦር ወንጀል ክሶች መመስረቱ አስታውቋል፡፡
አሜሪካ መራሽ ምዕራባዊ የኔቶ አባል ሃገራትም ለዩክሬን የሚያደርጉትን ወታደራዊ ድጋፍ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ሃገራቱ ድጋፍ ከማድረግ በዘለለ የሚያደርጉት ተሳትፎ ካለ መብረቃዊ ጥቃትን ለመፈጸም ዝግጁ ስለመሆኗ ሩሲያ መግለጿ ይታወሳል፡፡
ይህ በአንዲህ እያንዳ የአውሮፓ ኅብረት ሩሲያ ለፖላንድና ቡልጋሪያ ጋዝ አልሸጥም ማለቷን አውግዟል፡፡
የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ለየን እንዳሉት ይህ ሩሲያ የማታስተማምን የንግድ አጋር መሆኗን ነው የሚያሳየው፡፡
ሩሲያ በበኩሏ ይህን እርምጃ የወሰድኩት ወዳጅ ያልሆኑ አገራት ለማቀርብላቸው ጋዝ ክፍያቸውን በሩብል እንዲያደርጉ ያሳለፍኩትን ውሳኔ ፖላንድና ቡልጋሪያ ስላላከበሩት ነው ብላለች፡፡