ሩሲያ አሜሪካ ለዩክሬን የሰጠችውን የረጅም ርቀት ሮኬት ስርዓት አወደምኩ አለች
ባለፉት 15 ቀናት በተካሄደ ውጊያ ሩሲያ “አሜሪካ ሰራሹን ሒማርስ ሮክትን ጨምሮ የመሳሪየ መጋዝን አውድሜያለሁ” ብላለች
የዩክሬን ጦር ከአሜሪካ የተበረከተላትን የረጅም ርቀት ሮኬት ስርዓት መጠቀም መጀመሩን ገልጻ ነበር
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አሜሪካ ለዩክሬን የሰጠችውን የረጅም ርቀት ሮኬት ስርዓት ማውደሙን አስታወቀ።
ሚኒስቴሬ ባወጣው መግለጫ፤ ለዩክሬን ከተበረከቱ አሜሪካ ሰራሽ (HIMARS) የረጅም ርቀት ሮኬት ስርዓት ውስጥ አራት ማስወንጨፊያዎች አንድ ድጋፍ ሰጪ መኪና መውደሙን አሰታውቋል።
የረጅም ርቀት ሮኬት ማስወንጨፊያዎቹ የወደሙት ባሳለፍነው ሶስት ሳምነታት በዩክሬን ውስጥ በተደረገ ውጊያ መሆኑንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ለ15 ቀናት በአየር እና በመድር በመታገዝ በተደረገው ውጊያ (HIMARS) የረጅም ርቀት ሮኬት ስርዓት በተጨማሪ አንድ ዩክሬን የጦር መሳሪያ ማከማቻ ማውደሙንም የሩሲያ ጦር አስታውቋል
የዩክሬን ጦር ከአሜሪካ የተበረከተለትን የረጅም ርቀት የሮኬት ስርዓት በውጊያ ላይ መጠቀም መጀመሩን ከቀናት በፊት የሀገሪቱ ጦር አመራር ማስታቁ ይታወሳል።
የዩክሬን ጦር ከአሜሪካ የተቀበለውን (HIMARS) የሮኬት ስርዓት በዛፖሪዥያ ክልል ሲጠቀም የሚያሳይ ቪዲዮ ለቋል። በአንጻሩ የሩሲያ ጦር በቼርኒጎች፣ በሰኒይ እና በክሄርሰን ክልሎች የሚያደርገውን የአየር ድብደባ ማጠናከሩ ተነግሯል።
አሜሪካ ባሳለፍነው አርብ ለዩክሬን ተጨማሪ አራት (HIMARS) የሮኬት ስርዓት እንዲሁም 520 አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ጥይቶችን እንምትሰጥ አሰታውቃ ነበር።